ለወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በሙሉ

ስኳር ኮርፖሬሽን በቅርቡ ተቋርጦ የነበረውን የወልቃይት የስኳር ልማት ፕሮጀክት ሥራ ለማስቀጠል ለፕሮጀክቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የሚከተለውን ጥሪ ያስተላልፋል፡፡

የፕሮጀክቱ ሠራተኞች የሆናችሁና በመቀሌ ከተማና አካባቢው እንዲሁም በዳንሻ ከተማና አካባቢው የምትገኙ በሙሉ፤ ከየካቲት 10 እስከ የካቲት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት መቀሌ በሚገኘው የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ወይም በዳንሻ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ጠዋት ከ3 እስከ 6 ሰዓት፤ ከሰዓት በኋላ ከ7 ተኩል እስከ 10 ሰዓት ድረስ የፕሮጀክቱ ሠራተኛ መሆናችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በአካል ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ፣

በተመሳሳይ መምሪያ ኃላፊዎችና ከዚያ በላይ የሆናችሁ የሥራ ኃላፊዎች በሙሉ ረቡዕ የካቲት 10 ቀን 2013 ዓ.ም ጠዋት 3 ሰዓት ላይ በስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት ተገኝታችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ ኮርፖሬሽኑ እያሳሰበ፣ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ሪፖርት የማያደርጉ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ ያሳውቃል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ይህ ማስታወቂያ በፕሮጀክቱ ሳይት የሚገኙትንና ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት በአካል ተገኝተው ሪፖርት ያደረጉትን ሠራተኞች አይመለከትም፡፡

ስኳር ኮርፖሬሽን

Related posts