ስኳር ኮርፖሬሽን በግብር ክፍያ በፕላቲኒየም ደረጃ እውቅና አገኘ

  • የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካም በወርቅ ደረጃ እውቅና ተሰጥቶታል

በፌደራል ግብር ከፋዮች እውቅናና ሽልማት ሥነ ስርዓት ላይ ስኳር ኮርፖሬሽን በፕላቲኒየም ደረጃ እውቅና አገኘ፡፡ ሽልማቱን የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ መስከረም 7/2013 ዓ.ም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እጅ ተቀብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ በወርቅ ደረጃ እውቅና ከተሰጣቸው ግብር ከፋዮች መካከል አንዱ ሆኖአል፡፡

በእውቅናና ሽልማት ሥነ ስርዓቱ ላይ 20 ግብር ከፋዮች በፕላቲኒየም ደረጃ፣ 60 ግብር ከፋዮች በወርቅ እንዲሁም 120 ግብር ከፋዮች በብር ደረጃ እውቅና አግኝተዋል።

ሁለተኛው ዙር የፌደራል ግብር ከፋዮች የእውቅናና ሽልማት ሥነ ስርዓት በተካሄደበት ወቅት ታማኝ ግብር ከፋዮች በመንግሥት ተቋማት ቅድሚያ አገልግሎት እንዲሰጣቸው የሚያደርግ አሰራር እንዲዘረጋ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መመሪያ ሰጥተዋል።

Related posts