በምርምር የተገኙ አራት ሀገር በቀል የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎች እውቅና አገኙ

ዶ/ር ኢሳያስ ጠና ጋሻው
ዶ/ር ኢሳያስ ጠና ጋሻው

በስኳር ኮርፖሬሽን በምርምርና ልማት ዋና ማዕከል አማካይነት በከፍተኛ ተመራማሪ ዶ/ር ኢሳያስ ጠና ጋሻው በምርምር የተገኙ አራት ሀገር በቀል የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎች በሀገራችን የስኳር ኢንደስትሪ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በብሔራዊ ዝርያ አጽዳቂ ኮሚቴ ግንቦት 23/2011 ዓ.ም. እውቅና አግኝተው ተመዝግበዋል፡፡

ዝርያዎቹ ካላቸው በርካታ ከፍተኛ ጠቀሜታ ውስጥ የሚከተሉት በዋነኛነት ይጠቀሳሉ፡፡

  1. ለተለያዩ ሸንኮራ አገዳ አብቃይ ሥነ ምህዳሮች ተስማሚ መሆናቸው፣
  2. ከፍተኛ የአገዳ ምርትና የስኳር ይዘት ያላቸው መሆኑ (ከነባር ዝርያዎች በተሻለ ሁኔታ ከ20-30 በመቶ አብላጫ ከፍተኛ የስኳር ምርት መስጠት ይችላሉ)፣
  3. ነባር የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎች ለአጨዳ ከሚወስድባቸው ረጅም ጊዜ (ከ18-22 ወራት) ጋር ሲነጻጸር የተሻሻሉት ዝርያዎች ከ13-14 ወራት ጊዜ ውስጥ መድረሳቸው፣
  4. በሽታዎችና ተባዮችን እንዲሁም አካባቢ ተኮር የሆኑ ችግሮችን መቋቋም መቻላቸው (specific adaptability)፣ (ለምሳሌ፡- ጨዋማነትን፣ ድርቅንና የውሀ ተፋሰስ ችግር ያለባቸውን ቦታዎች/waterlogged areas)

በምርምር የተገኙት አራት ሀገር በቀል የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎች በስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባና በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሰላም ሚኒስትር አማካሪ እና የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ አባል አቶ ካይዳኪ ገዛኸኝ ግንቦት 30/2011 ዓ.ም. መመረቃቸው ይታወሳል፡፡

Related posts

Leave a Comment