በከሰም ስኳር ፋብሪካ የማሻሻያ /ሞዲፊኬሽን/ ሥራዎች ተከናወኑ

በከሰም ስኳር ፋብሪካ በክረምት መደበኛ የጥገና ወቅት ከዲዛይን ችግር ጋር በተያያዘ በኬን ቴብል ላይ በተደጋጋሚ ይከሰት የነበረውን የሸንኮራ አገዳ ብክነት ለመቀነስና ለማስቀረት የሚያስችሉ ውጤታማ የማሻሻያ /ሞዲፊኬሽን/ ሥራዎች መከናወናቸው ተገለፀ፡፡

የፋብሪካው የቴክኒክ ቡድን ሠራተኞች በቡድን መስራት በመቻላቸው ኬንቴብሉን ለመጠገን /በሞዲፊክ/ ለመስራት ይባክን የነበረውን ጊዜ ማስቀረት ከመቻሉ በተጨማሪ ጥራቱን የጠበቀ የማሻሻያ ሥራ በማከናወን ይባክን የነበረውን የሸንኮራ አገዳ መቀነስና ማስቀረት ማስቻሉንም የስራ ክፍሉ ባለሙያ አቶ ሲሳይ ——? ? ? አክለው ገልጸዋል፡፡

እንደ አቶ ሲሳይ ገለጻ ባለፈው ዓመት ምንም አይነት አገልግሎት የማይሰጠውን አራት ቁጥር ኬንቴብል በዘንድሮ ምርት ዘመን ወደ አገልግሎት እንዲገባ የማድረግ ስራም ተከናውኗል፡፡

በቴክኒክ ቡድን የተሰሩ እነዚህ የማሻሻያ ስራዎች ፋብሪካው በምርት ዘመኑ ለማምረት ያቀደውን 793.836 ኩንታል ስኳር ያለምንም ብክነት ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ነው የተገለፀው፡፡
በፋብሪው የቴክኒክ ቡድን ሠራተኞችና ኃላፊዎች ያላሰለሰ ጥረትም የፋብሪካው የምርት ሒደት እንዳይስተጓጎል የሚያስችሉ በርካታ የማሻሻያ ስራዎች ከመከናወናቸው በተጨማሪ በኬን ቴብል ላይ የተከናወነው የማሻሻያ ሥራ የሸንኮራ አገዳ ብክነትን በእጅጉ መቆጣጠር እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

በሌላ ዜና የከሰም ስኳር ፋብሪካ በትምህርታቸው ብልጫ ውጤት ላስመዘገቡ የሰገንቶ ቀበሌ ት/ቤት ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡ በ2009 የትምህርት ዘመን ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል አብላጫ ውጤት በማስመዝገብ በደረጃ ላጠናቀቁ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች የማበረታቻ የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገው ጥቅምት 10 ቀን 2010 ዓ.ም ነው፡፡

የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተገኑ ገናሞ በዚሁ ጊዜ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት ፋብሪካው ለተማሪዎቹ የሚያደርገው ድጋፍ ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎች ወደፊት የፋብሪካው ተረካቢዎች መሆናቸውን ሥራ አስኪያጁ አመልክተው ለዚህም በርትተው መማር እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና መምህራን በበኩላቸው የከሰም ስኳር ፋብሪካ ለተማሪዎቹ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው በቀጣይም የፋብሪካው ተመሳሳይ ድጋፍ እንደማይለያቸው ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡

Related posts

Leave a Comment