አቶ ወዮ ሮባ አካኮ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ

ኮርፖሬሽኑን ከታህሳስ 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምረው ላለፉት ሦስት ወራት በተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት የመሩት አቶ ወዮ ሮባ ከመጋቢት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾመዋል፡፡

አቶ ወዮ ወደ ስኳር ኮርፖሬሽን ከመጡበት ከ2004 ዓ.ም. አንስቶ ለሰባት ዓመታት የኦፕሬሽንስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው የእርሻና የፋብሪካ ኦፕሬሽን ሥራዎችን መርተዋል፡፡

ወደ ኮርፖሬሽኑ ከመምጣታቸው አስቀድሞም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ አገልግለዋል፡፡

Related posts

Leave a Comment