ኢንቨስትመንት

የኢንቨስትመንት ዕድሎች እና የጋራ ማልማት (joint investment) መስኮች

መንግሥት የልማት ድርጅቶችን በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በርካታ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች በስኳር ኢንደስትሪ እና በተጓዳኝ ምርቶች ላይ በሽርክና (joint venture) እና በግል ኢንቨስትመንት ለመሰማራት ፍላጎታቸውን እያሳዩ ይገኛሉ፡፡ በእርግጥ ስኳር ኮርፖሬሽን በዘርፉ ለመሳተፍ ፍላጎት ካላቸው ኩባንያዎች ጋር በጋራ ኢንቨስትመንት ሞዳሊቲ ለመስራት አለም አቀፍ ማስታወቂያ አውጥቶ መንቀሳቀስ የጀመረው ከመስከረም 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ነው፡፡

በዚህ መሰረት እስከ ጥር 2011 ዓ.ም. ድረስ 30 ኩባንያዎች ከስኳር ኮርፖሬሽን ጋር በሽርክና ለመስራት የኩባንያቸውን አቅምና ማንነት የሚገልጽ ማስረጃ /ፕሮፋይል/ አቅርበው ከአንዳንዶቹ ጋር ውይይት ተደርጎ የመግባቢያ ሰነድና የጋራ ልማት ኮንትራት መፈራረም ተችሏል፡፡

በስኳርና በተጓዳኝ ምርቶች ላይ በጋራ ማልማት ወይም በግል ኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት የተፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎች

 •  የመንግሥት ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፍላጎትና የፖለቲካ ቁርጠኝነት፣
 • በሀገሪቱ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ መሰረት የተመቻቹ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች/Incentives ፣
 • የሀገሪቱ የምጣኔ ሃብት እድገት፣
 • የተትረፈረፈ የተፈጥሮ ሀብትና የሰው ኃይል፣

ኢትዮጵያ የሸንኮራ አገዳና የስኳር ተጓዳኝ ምርቶችን በስፋት ለማምረት፡-

 •  በመሰኖ ሊለማ የሚችልና ለአገዳ ልማት ምቹ የሆነ 4 ሚሊዮን ሄክታር ለም መሬት
 • ተስማሚ የአየር ንብረት
 • ለመስኖ ልማት የሚውሉ በርካታ ወንዞች
 • ከፍተኛ የአገዳ ምርታማነት እና
 • ሰፊ ቁጥር ያለው አምራች የሰው ኃይል አላት፡፡
 • ከሸንኮራ አገዳ ምርታማነት አኳያም ሀገሪቱ በተፈጥሮ የታደለችው የአየር ንብረትና ለም መሬት ለአገዳ ልማት ተስማሚ በመሆኑ በአማካይ በ15 ወራት በሄክታር 1 ሺ 620 ኩንታል አገዳ ይመረታል፡፡ ይህ አሃዝ በአለምአቀፍ የሸንኮራ አገዳ ምርታማነት ማሳያ ደረጃ መሰረት ሲሰላ በኢትዮጵያ በሄክታር በወር 108 ኩንታል አገዳ ማምረት ይቻላል፡፡ በአለምአቀፍ ደረጃ በሄክታር በተመሳሳይ ጊዜ ከሚመረተው የሸንኮራ አገዳ ምርት ጋር ሲነጻጸርም የ23 ኩንታል ብልጫ አለው፡፡
 • የመሠረተ ልማት አውታሮች ዝርጋታ (ትላልቅ ግድቦችና የመስኖ መሰረተ ልማት፣ መንገድ፣ የአየር ማረፊያ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ ቴሌኮሚዩኒኬሽን ወዘተ)፣
 • 102 ሺ ሄክታር በአገዳ የተሸፈነ መሬት፣
 • በሀገር ደረጃ ስኳር እና ኢታኖል በማምረት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ያስቆጠረ ልምድ፣
 • ወደ ሥራ የገቡና በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ 10 አዳዲስ ግዙፍ የስኳር ፋብሪካዎች፣
 • እያደገ የመጣ የህብረተሰቡ የስኳር ፍላጐትና ከዚህ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ሰፊ የሀገር ውስጥ ገበያ፣
 • በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፉ የመጡ ስኳርን በግብዓትነት የሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች፣
 • ከፍተኛ የእንስሳት ሃብት (የእንስሳት መኖ ማቀነባበርና ማድለብ ይቻላል)፣

 የስኳር ዋንኛ ተረፈ ምርቶች (Major Sugar By-products)

 • ሞላሰስ (Molasses)
 • ኢታኖል (Ethanol)
 • ባጋስ (Bagasse)

 የሀገራችን ተሞክሮ በስኳር ተጓዳኝ ምርቶች (Sugar Co-products)

 •  የኤሌክትሪክ ኃይል (Electricity)
 • ፍራፍሬ (Fruits) ; Orange, Banana, Mango
 • የእንስሳት መኖ (Animal feed)
 • ከብት ማድለብ (Cattle Fattening)
 • ጥጥ (Cotton)
 • ሩዝ (Rice)
 • አኩሪ አተር (Soya bean)
 • ሰሊጥ (Sesame)
 • ስንዴ (Wheat)
 • ቦሎቄ (Haricot bean)
 • ማሾ (Mung bean)

በሽርክና (Joint venture) ወይም በግል ኢንቨስት የሚደረግባቸው መስኮች

 •  የስኳር ፕሮጀክቶች ግንባታ፣
 • ስኳር ፋብሪካ የማስተዳደርና ኦፕሬሽን የመምራት ሥራ፣
 • የኢታኖል ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ የማስተዳደርና ኦፕሬሽን የመምራት ሥራ፣
 • የተለያዩ የስኳር ተጓዳኝ ምርቶች ልማት፣
 • የመስኖ ዝርጋታ፣ የመሬት ዝግጅት እና ሸንኮራ አገዳ ልማት ፕሮጀክቶች፣
 • የስኳር ፋብሪካ የመለዋወጫ እቃዎች ማምረቻ ኢንደስትሪ፣
 • የእንስሳት መኖ ልማትና ማድለብ ሥራ፣
 • የወረቀት ማምረቻ ፋብሪካ፣
 • የችፕቦርድ ማምረቻ ፋብሪካ፣
 • የአልክሆል መጠጥ ኢንደስትሪ፣
 • የስኳር ማሸጊያ ከረጢት/ጆንያ ማምረቻ ፋብሪካ፣
 • የቀለም ማምረቻ ፋብሪካ ወዘተ