ኮርፖሬሽኑ ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች አከበረ

ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን በማስመልከት በተደረገ የሥራ ጉብኝት ቁጥራቸው ከ50 በላይ የሆነ የኮርፖሬሽኑ ዋና መሥርያ ቤት ሴት ሠራተኞች ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካን ጎብኝተዋል፡፡ ጉብኝቱ በሴት ሠራተኞቹ ጥያቄ መሠረት የተከናወነ ነው ያሉት የኮርፖሬሽኑ ሴቶች እና ወጣቶች አገልግሎት ኃላፊ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ከበደ ከጉብኝቱ ሠራተኞቹ ጠቃሚ ልምድ እንዳገኙ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

ከጉብኝቱ ጎን ለጎን በተደረገ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም የማንጎ፣ የፓፓያ እና የሙዝ ችግኞች በፋብሪካው አካባቢ ተተክለዋል፡፡

Related posts