የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ስቲሪንግ ኮሚቴ የመተሐራና ወንጂ ሽዋ ስኳር ፋብሪካዎችን ጎበኘ

ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በአባልነት የሚገኙበትና በአምባሳደር ግርማ ብሩ የተመራ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ስቲሪንግ ኮሚቴ የመተሐራና ወንጂ ሽዋ ስኳር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የምርምር ማዕከልንና የስኳር አካዳሚን የሥራ እንቅስቃሴ ጥር 28/2013 ዓ.ም ጎብኝቷል።

ኮሚቴው ከጉብኝቱ በኋላ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወዮ ሮባ፣ የፋብሪካዎቹ ኮር ማኔጅመንትና የሠራተኛ ማኅበር ተወካዮች እንዲሁም የኮርፖሬሽኑ መሠረታዊ የሠራተኛ ማኅበር ሰብሳቢ በተገኙበት ባደረገው ውይይት የፋብሪካዎቹን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ኢንደስትሪውን ትርፋማ ማድረግ እንደሚገባ አሳስቦ፣ ከፋብሪካዎቹ አቅም በላይ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቆአል።

በተጨማሪም ኮሚቴው ጥር 29/2013 ዓ.ም. በኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወዮ ሮባ የቀረበውን የስኳር ኢንደስትሪ የሪፎርም ሥራዎች የትኩረት አቅጣጫና የተመዘገቡ ውጤቶችን ገለፃም አዳምጦአል።

በመጨረሻም የሁለት ቀናት የሥራ ቆይታውን አስመልክቶ የሥራ አቅጣጫና መመሪያ ሠጥቶአል።

Related posts