የስኳር ኮርፖሬሽን ሠራተኞች በአረንጓዴ አሻራ ቀን የራሳቸውን አሻራ አኖሩ

በሀገር አቀፍ ደረጃ “የአረንጓዴ አሻራ ቀን” በሚል መሪ ቃል ሁለት መቶ ሚሊየን ችግኞች ለመትከል የተካሄደውን ሕዝባዊ ንቅናቄ ተከትሎ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባን ጨምሮ የዋናው መ/ቤት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች እንዲሁም የስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ዋና ሥራ አስኪያጆች የካ ሚሊኒየም ፓርክ አካባቢ በሚገኘው የደን ክልል ዛሬ ሐምሌ 22/2011 ዓ.ም. የጽድ፣ የግራር እና ሌሎች ሀገር በቀል እጽዋት ችግኞችን ተክለዋል፡፡

የተቋሙ ሠራተኞች አንድ ላይ በመሆን ችግኞችን ሲተክሉ የዛሬው ለስድስተኛ ጊዜ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም ለአምስት ጊዜያት ያህል በየካና ፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢዎች በሚገኙ የደን ክልሎች ችግኞችን ተክለዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ በየዓመቱ በችግኝ ተከላ እየተሳተፉ ካሉ ተቋማት በጸደቁ ችግኞች ብዛት ግንባር ቀደም በመሆንም በየካ ክፍለ ከተማ የተፈጥሮ ሃብት ልማት አጠቃቀምና ቁጥጥር የሥራ ክፍል አድናቆት ተችሮታል፡፡

በተመሳሳይ በዛሬው የአረንጓዴ አሻራ ቀን የስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በየተቋማቱ ቅጥር ግቢና በየአካባቢዎቹ ችግኞችን ሲተክሉ ውለዋል፡፡

Related posts

Leave a Comment