የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና ስልጠና ተካሔደ

የኮርፖሬሽኑ የሥነ ምግባርና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች አገልግሎት የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና ስልጠና ተካሄደ፡፡

የካቲት 29 እና 30 ቀን 2013 ዓ.ም በወንጂ  ስኳር አካዳሚ በተካሄደው የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ከወልቃይትና ተንዳሆ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የሥራ ክፍሎች በስተቀር ከሁሉም ስኳር ፋብሪካዎች፣ፕሮጀክቶችና ምርምርና ልማት ዋና ማእከል የተወከሉ የሥነ ምግባርና መልካም አስተዳደር የሥራ ክፍል ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በዕቅድ አፈጻጸም ግምገማው ላይ ስለተሻሻለው የፌዴራል የሥነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ፣ ስለ አዲሱ የሀብት ምዝገባ መመሪያ፣ የአሰራር ስርዓትና አስቸኳይ የሙስና መከላከልን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የኮርፖሬት ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ዘመድኩን ተክሌ ተገኝተው የሥነ ምግባርና መልካም አስተዳደር የሥራ ክፍል ባለሙያዎች ኮርፖሬሽኑ የጀመረውን የለውጥ ጉዞ ከግብ ለማድረስ በሥነ ምግባር የታነጸ ሠራተኛ በመፍጠርና አሰራሮችን በመዘርጋት ሙስና ከመከሰቱ በፊት መከላከል ላይ ማተኮር እንደሚገባቸው  አሳስበው በዚህ ረገድም ኮርፖሬሽኑ  አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ  አመልክተዋል፡፡

Related posts