የኢትዮጵያ ስኳር አካዳሚ

ኳር ኮርፖሬሽን ሀገሪቱን በ2016ዓ.ም ከዓለም ምርጥ ስኳር አምራች አገራት ተርታ ለማሰለፍ ሁለንተናዊ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የሚያከናውናቸውን ዘርፈብዙ እንቅስቃሴዎች በሰው ኃይል፣ በአሰራር እና በቴክኖሎጂ ለማገዝ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ የጥናት እና ምርምር ማዕከል በ2009 ዓ.ም ስኳርአካዳሚ አቋቁሟል፡፡ አካዳሚው ኮርፖሬሽኑ ያለበትን የዕውቀት፣ የአመለካከት እና የክሂሎት ክፍተቶች ይሞላል ተብሎም ከወዲሁ ታኖበታል፡፡

አካዳሚው የተጣለበትን ከፍተኛ ኃላፊነት ለመወጣትም የአጭር እና የረዥም ጊዜ ዕቅድ ነድፎ እየተገበረ የሚገኝ ሲሆን የሚሰጠው ሥልጠናም ንድፈሐሳብንከተግባር ያጣመረ ነው፡፡
ለአገሪቱ የመጀመሪያው ስኳር ፋብሪካ በነበረው በወንጂ ስኳር ፋብሪካ ግቢ ውስጥ የተመሠረተው የኢትዮጵያ ስኳር አካዳሚ ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎቹንበጣም አነስተኛ በሆነ ወጪ ለመማርያ ፣ ለመኝታ፣ ለቤተመጻሕፍት እና ሌሎች አገልግሎቶች ምቹ በሆነ መልኩ አድሷል፡፡

አካዳሚው የቀድሞዎቹን የወንጂ እና የሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች በማሻሻል ለተግባር ተኮር ስልጠና ምቹ እንዲሆኑ እንዲሁም አዳዲስ ግንባታዎችን በማከናወን በርካታሥራዎች አጠናቋል በዚህም

 • የፋብሪካዎቹን የቀድሞ ቢሮዎች ወደ ማሰልጠኛ ክፍሎች እንዲቀየሩ ተደርጓል፡፡ ይህም አካዳሚውን እስከ 250 ሰልጣኞችን በአንድ ጊዜ ለመቀበል አስችሎታል፤
 • እያንዳንዳቸው አራት ሰልጣኞችን የማስተናገድ አቅም ያላቸው 50 የማደሪያ ክፍሎች ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፤
 • ደረጃውን የጠበቀ አንድ ዘመናዊ የምግብ ማብሰያ ክፍል እና የመመገቢያ አዳራሽ ግንባታን አጠናቆ ውስጣዊ አደረጃጀቱ በሒደት ላይ ይገኛል፣
 • የቤተመጻሕፍት አገልግሎት የማደራጀት ሥራ ተከናውኗል እንዲሁም
 • የቀድሞውን የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ወርክ ሾፕ ለስልጠና ምቹ በሚሆንበት መልኩ የማደራጀት ሥራም በሒደት ላይ ይገኛል፡፡
 • ስኳር አካዳሚው የእርሻ፣ የፋብሪካና የሥራ አመራር ሥልጠናዎችን ከስኳር ፋብሪካዎች፣ ስኳር ልማት ፕሮጀክቶችና ከኮርፖሬሽኑ ዋና መስርያ ቤት ለተውጣጡ አመራር አባላትና ባለሙያዎች ይሠጣል፡፡
 • ካዳሚው በአጠቃላይ አስራዘጠኝ መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች ያለው ሲሆን ስልጠና የሚሰጠውም በሚከተሉት የተምህርት መስኮች ዙሪያ ነው:-
 1. Irrigation and Drainage
 2. Managerial Skill
 3. Haulage High bed trucks operation
 4. Machinery safety and Technical Training
 5. Transformational Leadership
 6. Supervisory Management
 7. Compliance Management and compliant handling
 8. Sugar cane harvesting and fleet management
 9. Insurance Policy
 10. Chemical Control
 11. Cost Management
 12. Finance and non finance managers
 13. Health sector Transformation
 14. Material /Supply Management

Related posts

Leave a Comment