የኮርፖሬሽኑ ስራ አመራር ቦርድ በስኳር ልማት ዘርፍ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ስብሰባ አካሄደ

የስኳር ኮርፖሬሽን ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በቅርቡ የተሾሙት ክቡር አምባሳደር ግርማ ብሩ “በስኳር ልማት ዘርፍ ወቅታዊ ሁኔታ፣ ችግሮች እና መፍትሔ የሚፈልጉ ጉዳዮች” በሚል ርዕስ ዙሪያ ከኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራር አባላት ጋር ሐሙስ መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም የመጀመሪያ ስብሰባቸውን አካሄዱ። አምባሳደር ግርማ በኮርፖሬሽኑ ሕንጻ ሶስተኛ ፎቅ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ባደረጉት በዚሁ የመጀመሪያ ስብሰባ ከስኳር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮች ጋር ትውውቅ ያደረጉ ሲሆን አቶ ማሞ ምህረቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እንዲሁም አቶ ፈቃዱ አጎናፍር ከኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የስኳር ኮርፖሬሽን ስራ አመራር ቦርድ አዲስ አባላት ሆነው ተመድበዋል። በዚሁ ስብሰባ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና…

የኮርፖሬሽኑ የስምንት ወራት የመሰረታዊ ሥራዎች ዕቅድ አፈጻጸም አበረታች መሆኑ ተገለጸ

የስኳር ኮርፖሬሽን የያዝነው በጀት ዓመት የስምንት ወራት የመሰረታዊ ሥራዎች ዕቅድ አፈጻጸም አበረታች መሆኑ ተገለጸ። ይህ የተገለጸው ከኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት፣ ከስኳር ፋብሪካዎችና ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የተውጣጡ አመራር አካላት እና የኮርፖሬሽኑ የመሠረታዊ ሠራተኛ ማኅበር ተወካዮች በቢሾፍቱ ከተማ ከመጋቢት 1 – 3 ቀን 2103 ዓ.ም በተካሄደው የኮርፖሬሽኑ የስምንት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ነው። የኮርፖሬሽኑ የስምንት ወራት የመሰረታዊ ሥራዎች ዕቅድ አተገባበር ግምገማ መድረክ ከተወያዬባቸው አጀንዳዎች መካከልም የስኳር ፋብሪካዎች የስምንት ወራት የምርት ዕቅድ አፈጻጸም፣ በለስ ስኳር ፋብሪካን ወደ ስራ በማስገባት ላይ በስፋት ያተኮረ የፕሮጀክት ሥራዎች የስምንት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም፣ የሪፎርም ሥራዎች ዕቅድ አፈጻጸም፣የኮርፖሬሽኑ…

የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና ስልጠና ተካሔደ

የኮርፖሬሽኑ የሥነ ምግባርና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች አገልግሎት የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና ስልጠና ተካሄደ፡፡ የካቲት 29 እና 30 ቀን 2013 ዓ.ም በወንጂ  ስኳር አካዳሚ በተካሄደው የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ከወልቃይትና ተንዳሆ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የሥራ ክፍሎች በስተቀር ከሁሉም ስኳር ፋብሪካዎች፣ፕሮጀክቶችና ምርምርና ልማት ዋና ማእከል የተወከሉ የሥነ ምግባርና መልካም አስተዳደር የሥራ ክፍል ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በዕቅድ አፈጻጸም ግምገማው ላይ ስለተሻሻለው የፌዴራል የሥነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ፣ ስለ አዲሱ የሀብት ምዝገባ መመሪያ፣ የአሰራር ስርዓትና አስቸኳይ የሙስና መከላከልን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የኮርፖሬት ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ዘመድኩን ተክሌ ተገኝተው…

የኮርፖሬሽኑ ሕግና ኢንሸራንስ ጉዳዮች አለአግባብ በሥር ፍ/ቤት የተወሰነ የ18 ሚሊዮን ብር ክፍያን አስሻረ

የኮርፖሬሽኑ ሕግና ኢንሸራንስ ጉዳዮች የሥራ ክፍል ስኳር ኮርፖሬሽን በአዳማ ከተማ ተከራይቶት የነበረን መጋዘን  አስመልክቶ አለአግባብ በሥር ፍ/ቤት የተወሰነበትን የ18 ሚሊዮን ብር ክፍያ አስሻረ፡፡ ​የስኳር ኮርፖሬሽን ግብይት ዘርፍ ከውጪ  ላስገባው ስኳር  ማከማቻ እንዲሆን በአዳማ ከተማ ተከራይቶት የነበረው የግለሠብ መጋዘን በሌሊት ተደርምሶ በመገኘቱ የመጋዘኑ ባለቤት በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት አዳማ ምድብ ችሎት የፍትሐብሔር ክስ  በመመስረቱ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ተመልክቶ ለግለሠቡ ጠቅላላ ወጪን ጨምሮ 18 ሚሊዮን ብር እንዲከፈል ወስኖ ጉዳዩ በአፈጻጸም ሒደት ላይ የነበረ እንደነበር ታውቋል። ይሁንና የኮርፖሬሽኑ ሕግና ኢንቩራንስ የሥራ ክፍል  ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረብና አፈፃፀሙን በማሣገድ ከሁለት ዓመት ክትትል በኋላ ይግባኝ ሰሚው…

ኮርፖሬሽኑ ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች አከበረ

ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን በማስመልከት በተደረገ የሥራ ጉብኝት ቁጥራቸው ከ50 በላይ የሆነ የኮርፖሬሽኑ ዋና መሥርያ ቤት ሴት ሠራተኞች ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካን ጎብኝተዋል፡፡ ጉብኝቱ በሴት ሠራተኞቹ ጥያቄ መሠረት የተከናወነ ነው ያሉት የኮርፖሬሽኑ ሴቶች እና ወጣቶች አገልግሎት ኃላፊ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ከበደ ከጉብኝቱ ሠራተኞቹ ጠቃሚ ልምድ እንዳገኙ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ ከጉብኝቱ ጎን ለጎን በተደረገ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም የማንጎ፣ የፓፓያ እና የሙዝ ችግኞች በፋብሪካው አካባቢ ተተክለዋል፡፡

ለወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በሙሉ

ስኳር ኮርፖሬሽን በቅርቡ ተቋርጦ የነበረውን የወልቃይት የስኳር ልማት ፕሮጀክት ሥራ ለማስቀጠል ለፕሮጀክቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የሚከተለውን ጥሪ ያስተላልፋል፡፡ የፕሮጀክቱ ሠራተኞች የሆናችሁና በመቀሌ ከተማና አካባቢው እንዲሁም በዳንሻ ከተማና አካባቢው የምትገኙ በሙሉ፤ ከየካቲት 10 እስከ የካቲት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት መቀሌ በሚገኘው የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ወይም በዳንሻ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ጠዋት ከ3 እስከ 6 ሰዓት፤ ከሰዓት በኋላ ከ7 ተኩል እስከ 10 ሰዓት ድረስ የፕሮጀክቱ ሠራተኛ መሆናችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በአካል ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ፣ በተመሳሳይ መምሪያ ኃላፊዎችና ከዚያ በላይ የሆናችሁ የሥራ ኃላፊዎች በሙሉ ረቡዕ የካቲት 10 ቀን 2013…

የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ስቲሪንግ ኮሚቴ የመተሐራና ወንጂ ሽዋ ስኳር ፋብሪካዎችን ጎበኘ

ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በአባልነት የሚገኙበትና በአምባሳደር ግርማ ብሩ የተመራ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ስቲሪንግ ኮሚቴ የመተሐራና ወንጂ ሽዋ ስኳር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የምርምር ማዕከልንና የስኳር አካዳሚን የሥራ እንቅስቃሴ ጥር 28/2013 ዓ.ም ጎብኝቷል። ኮሚቴው ከጉብኝቱ በኋላ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወዮ ሮባ፣ የፋብሪካዎቹ ኮር ማኔጅመንትና የሠራተኛ ማኅበር ተወካዮች እንዲሁም የኮርፖሬሽኑ መሠረታዊ የሠራተኛ ማኅበር ሰብሳቢ በተገኙበት ባደረገው ውይይት የፋብሪካዎቹን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ኢንደስትሪውን ትርፋማ ማድረግ እንደሚገባ አሳስቦ፣ ከፋብሪካዎቹ አቅም በላይ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቆአል። በተጨማሪም ኮሚቴው ጥር 29/2013 ዓ.ም. በኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወዮ ሮባ የቀረበውን…

“የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ በጦር ጀት ተደብድቧል” ተብሎ የቀረበው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው

አዲስ አበባ ህዳር 6/2013 (ኢዜአ) ዘራፊው የህወሓት ቡድን “የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ በጦር ጀት ተደብድቧል” በማለት ያናፈሰው ወሬ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ መሆኑን የስኳር ኮርፖሬሽን አስታወቀ። የአጥፊው የህወሓት ቡድን መሪ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ በጦር ጀት ተደብድቧል ሲሉ ትናንት ምሽት የራሳቸው ልሳን በሆነው ሚዲያ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጉዳዩን ለማጣራት የስኳር ኮርፖሬሽን የፕሮጀክት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብርሃም ደምሴን አነጋግሯል። አቶ አብርሃም በወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ላይ በመንግስት የጦር ጀት ድብደባ ተፈፅሟል ተብሎ በዘራፊው የህወሓት ቡድን የሚነዛው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን አረጋግጠዋል። የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት በስኳር ኮርፖሬሽን የሚተዳደርና ንብረትነቱም…

ለስኳር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮች ሥልጠና ተሰጠ

የክህሎት፣ የአመራር ጥበብና ብቃት እንዲሁም የሥራ ተነሳሽነትን የሚያሳድግ ሥልጠና ለስኳር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮች ተሰጠ፡፡ ሥልጠናው ከመፈጸምና ማስፈጸም አቅም፣ ከሥልጠና ፍላጎትና ከስኳር ኢንደስትሪው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተገናዝቦ የተዘጋጀ ነው፡፡ በስኳር አካዳሚ አዘጋጅነት በአዳማ ካኔት ሆቴል ከጥቅምት 23-26/2013 ዓ.ም ድረስ የተካሄደው ይህ ሥልጠና በTransformational Leadership፣ Emotional Intelligence፣ Reform Management and Role of leadership፣ Quality Management System & Paradigm Shift እና Finance for Non-Financial Managers የሥልጠና ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነበር፡፡ የሥልጠናውን መርሃ ግብር ያስጀመሩት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ ባደረጉት ንግግር፣ ሥልጠናው ኮርፖሬሽኑ በ2012 በጀት ዓመት ያስመዘገበውን አበረታች ውጤትና ይህን…

በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ አመታዊ የፕላንት ፕሮሰስ ኮንፈረንስ ተካሄደ፡፡

የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች እውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ አመታዊ የፕላንት ፕሮሰስ ኮንፈረንስ ከመስከረም 21-23/2ዐ13 ዓ.ም ድረስ ተካሄደ፡፡ በፋብሪካው የሲኒማ አዳራሽ ለሦስት ቀናት በተካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወዮ ሮባ፣ በዋናው መ/ቤት የፕሮጀክት ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ደምሴና የወንጂ ሸዋ ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ካሳ ተስፋዬን ጨምሮ የፋብሪካው ም/ዋና ሥራ አስኪያጆች፣ የእርሻና የፋብሪካ ኦፕሬሽን ዘርፎች የሥራ ኃላዎችና ሠራተኞች እንዲሁም ከፍተኛ ተመራማሪዎች፣ የሕብረት ሥራ ማህበር ኃላፊዎች፣ የዘርፍ ማህበር አመራሮች እና ሌሎች ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡ መርሃ ግብሩን በንግግር ያስጀመሩት…