የኢትዮጵያ ስኳር አካዳሚ

ኳር ኮርፖሬሽን ሀገሪቱን በ2016ዓ.ም ከዓለም ምርጥ ስኳር አምራች አገራት ተርታ ለማሰለፍ ሁለንተናዊ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የሚያከናውናቸውን ዘርፈብዙ እንቅስቃሴዎች በሰው ኃይል፣ በአሰራር እና በቴክኖሎጂ ለማገዝ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ የጥናት እና ምርምር ማዕከል በ2009 ዓ.ም ስኳርአካዳሚ አቋቁሟል፡፡ አካዳሚው ኮርፖሬሽኑ ያለበትን የዕውቀት፣ የአመለካከት እና የክሂሎት ክፍተቶች ይሞላል ተብሎም ከወዲሁ ታኖበታል፡፡ አካዳሚው የተጣለበትን ከፍተኛ ኃላፊነት ለመወጣትም የአጭር እና የረዥም ጊዜ ዕቅድ ነድፎ እየተገበረ የሚገኝ ሲሆን የሚሰጠው ሥልጠናም ንድፈሐሳብንከተግባር ያጣመረ ነው፡፡ ለአገሪቱ የመጀመሪያው ስኳር ፋብሪካ በነበረው በወንጂ ስኳር ፋብሪካ ግቢ ውስጥ የተመሠረተው የኢትዮጵያ ስኳር አካዳሚ ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎቹንበጣም አነስተኛ በሆነ ወጪ…