ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ

የኦሞ ወንዝን በሚያዋስኑ በካፋና ቤንች ማጂ ዞኖች የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አባባ 874 ከ.ሜ ይርቃል፡፡ ፋብሪካው ጥቅምት 4 ቀን 2011 ዓ.ም. በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ተመርቆ ሥራ ጀምሯል፡፡ የፋብሪካው ግንባታ በይፋ የተጀመረው መጋቢት 2/2008 ዓ.ም ከቻይና ልማት ባንክ በተገኘ ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ነው፡፡ ኮምፕላንት በተባለ የቻይና ኩባንያ የተገነባው ይህ ፋብሪካ በቀን ከ8,000 አስከ 10,000 ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም ያለው ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡ እጅግ ዘመናዊ ከመሆኑ አንጻርም የአለም ገበያ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ ጥሬ ስኳር (Raw sugar)፣ ነጭስኳር (Plantation white sugar) እና የተጣራ ስኳር…

መተሐራ ስኳር ፋብሪካ

ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በመቀጠል በሆላንዱ ኤች ቪ ኤ ተገንብቶ በ1962 ዓ.ም. ወደ ስራ የገባው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በ200 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ከ10 ሺ ሄክታር በላይ በሸንኮራ አገዳ የተሸፈነ መሬት ያለው ይህ ፋብሪካ በዓመት 1.3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም አለው፡፡ ፋብሪካው ባካሄደው የማስፋፊያ ፕሮጀክት የኤታኖል ፋብሪካ ገንብቶ ከ2003 ዓ.ም. አጋማሽ ጀምሮ ኤታኖል በማምረት ላይ ይገኛል፡፡ ኤታኖል የማምረት ዓመታዊ አቅሙም በአመት እስከ 12.5 ሚሊዮን ሊትር ይደርሳል፡፡ በሌላ በኩል “ባጋስ” ተብሎ ከሚጠራው የሸንኮራ አገዳ ገለባ 9 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት የራሱን የኃይል ፍላጎት እያሟላ የሚገኝ እድሜ ጠገብ…

ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ

የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምዕራብ 350 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በአባይ ጮመን ወረዳ በፊንጫአ ሸለቆ ውስጥ ልዩ ስሙ አገምሳ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ ይገኛል፡፡ የፊንጫአ ሸለቆ ለስኳር ኢንዱስትሪ ተስማሚ ሆኖ በመገኘቱ ቡከርስ አግሪካልቸራል ኢንተርናሽናል ሊሚትድ በተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ ከ1970 ዓ.ም. ጀምሮ የቦታው አዋጭነት፣ የመሬቱ አቀማመጥና የአፈር ይዘት ሁኔታ ላይ ዝርዝር ጥናት ተካሂዶ አዋጭነቱ ተረጋገጠ፡፡ የአፍሪካ ልማት ባንክና የአፍሪካ ልማት ፈንድ፣ የስውዲን፣ የአውስትራሊያና የስፔን መንግሥታት እንዲሁም የሀገር ውስጥ ባንኮች የፋይናንስ ምንጮች መሆናቸው ተረጋግጦ የፕሮጀክቱ ግንባታ    ጥር 1981 ዓ.ም. ተጀመረ፡፡ ከፊንጫአ ወንዝ በስተምዕራብ እና ምስራቅ…

ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ

በአዋሽ ተፋሰስ ዝቅተኛ አካባቢ በአፋር ክልል በ25 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት የሚጠቀመው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በ670 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በግዙፍነቱ እና በተሻለ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነቱ ጭምር ከሌሎቹ ነባር ስኳር ፋብሪካዎች የሚለየው ይህ ፋብሪካ ከሀገሪቱ መዲና አዲስ አበባ በስተምስራቅ ወደ ጅቡቲ የሚወስደውን መንገድ ተከትሎ ከጅቡቲ ወደብ በ300 ኪ.ሜ ርቅት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ምቹ ሁኔታም ወደፊት የፋብሪካውን ምርት ወደ ውጭ ለመላክ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በ1998 ዓ.ም. የፕሮጀክት ሥራው የተጀመረው የግዙፉ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ይዞታ በሚሌ፣ በዱብቲ፣ በአሳኢታ እና በአፋምቦ ወረዳዎች ውስጥ ይገኛል፡፡ OIA (Overseas…

አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ

የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በምዕራብ ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ፣ በቡኖ በደሌና በጅማ ዞኖች በዲዴሳ ሸለቆ ውስጥ ከአዲስ አበባ ነቀምት በደሌ በሚወስደው መንገድ በ395 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የአካባቢው ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ በአማካይ 1350 ሜትር ሲሆን፣ የአየር ሁኔታው ሞቃታማ ነው፡፡ አመታዊ አማካይ የዝናብ መጠኑም 1400 ሚሊ ሊትር ይደርሳል፡፡ የዝናብ ሥርጭቱ ደግሞ ከግንቦት እስከ ጥቅምት ይዘልቃል፡፡ በአብዛኛው ጥቁርና አልፎ አልፎ ቀይ ቡናማ አፈር የሚገኝበት ይህ አካባቢ ከአየር ንብረቱ ጋር ተዳምሮ ለሸንኮራ አገዳ ልማት ምቹና ተስማሚ እንዲሆን አስችሎታል፡፡ AL-Habasha Sugar Mills PLC ከተባለ የፓኪስታን ኩባንያ በ2005 ዓ.ም. በግዢ ወደ ስኳር…

ከሰም ስኳር ፋብሪካ

በአፋር ክልል በዞን ሦሥት አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች በከሰም ቀበና ሸለቆ ውስጥ ውስጥ የሚገኘው የከሰም ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ 250 ኪ.ሜ፣ ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ደግሞ 50 ኪ.ሜ. ያህል ይርቃል፡፡ ለመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የማስፋፊያ ፕሮጀክት አካል ሆኖ በ2003 ዓ.ም. የግንባታው ቅድመ ዝግጅት የተጀመረው የከሰም ስኳር ፋብሪካ ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ካለው ርቀትና ከአዋጪነት አንፃር ተጠንቶ ኋላ ላይ ራሱን ችሎ እንደ አንድ የስኳር ፋብሪካ እንዲቋቋም ተደረገ፡፡ ከቻይና ልማት ባንክ በተገኘ 123 ሚሊዮን ዶላር ብድር ኮምፕላንት በተባለ የቻይና ኩባንያ የተገነባው የከሰም ስኳር ፋብሪካ በ2007 ዓ.ም. መጨረሻ የሙከራ ምርቱን አጠናቆ ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ በመደበኛ…

ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ

በደቡብ ኦሞ ዞን በሰላማጎ ወረዳ የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አባባ 825 ኪ.ሜ ይርቃል፡፡ ከቻይና ልማት ባንክ በተገኘ 6.67 ቢሊዮን ብር ብድር ሐምሌ 2007 ዓ.ም. ግንባታው በይፋ የተጀመረው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ መጋቢት 14/2009 ዓ.ም. የሙከራ ምርቱን ካሳካ  በኋላ ወደ መደበኛ ምርት ተሸጋግሯል፡፡ ኮምፕላንት በተባለ የቻይና ኩባንያ የተገነባው ይህ ፋብሪካ በቀን ከ8,000 አስከ 10,000 ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም ያለው ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡

ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ

በሀገራችን የስኳር ፋብሪካ ታሪክ ፋና ወጊ የሆነው የወንጂ ስኳር ፋብሪካ በ1946 ዓ.ም. ግንባታው ተጠናቆ ማምረት የጀመረ ሲሆን፣ የሸዋ ስኳር ፋብሪካ ደግሞ እዛው ወንጂ ላይ በ1955 ዓ.ም. ተመርቆ ስራ የጀመረ ሌላኛው ስኳር ፋብሪካ ነው፡፡ ሁለቱም ስኳር ፋብሪካዎች ኤች ቪ ኤ በተባለ የሆላንድ ኩባንያ የተገነቡና በኩባንያውና በመንግሥት የጋራ ባለቤትነት በሽርክና የተቋቋሙ ነበሩ፡፡ በአንድ አስተዳደር ስር እየተዳደሩ ስኳር ያመርቱ የነበሩት ሁለቱ አንጋፋ ፋብሪካዎች በእርጅና ምክንያት ሥራቸውን እስካቆሙበት ጊዜ ማለትም ወንጂ እስከ 2004 ዓ.ም. እንዲሁም ሸዋ እስከ 2005 ዓ.ም. መጨረሻ ድረስ የነበራቸው አማካይ አመታዊ ስኳር የማምረት አቅም 75 ሺ ቶን ወይም 750  ሺ ኩንታል…

ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ኢንዱስትሪ

የሀገራችን ኢንዱስትሪ በኢኮኖሚው ውስጥየመሪነቱን ሚና እንዲጫወት የላቀ አስተዋጽኦካላቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱየስኳር ልማት ፕሮጀክት ነው። ኢትዮጵያ ይህንኤክስፖርት መር የሆነ የማኑፋክቸሪንግኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማስፋፋትና ምርታማነቱንለማሳደግ የሚያስችል ከፍተኛ የሰው ኃይልናየተፈጥሮ ሃብት አላት፡፡ በተለይም ሀገሪቱ ለሸንኮራ አገዳ ልማት ተስማሚአየር ንብረት፣ በመሰኖ ሊለማ የሚችል ሰፊየእርሻ መሬት (ከ500ሺ ሄክታር በላይ) እንዲሁም በቂ ውሃ ያላት በመሆኑ ዘርፉ የበለጠትኩረት እንዲሰጠው ተደርጓል፡፡ ከዚህ ባሻገር መንግሥት የሀገሪቱ ህዝቦች ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በሚከተለው የፖሊሲአቅጣጫ መሰረት በወንጂ ሸዋና መተሓራ ስኳር ፋብሪካዎች ብቻ ለረጅም ዓመታት ያህል ተወስኖ የቆየውን የስኳር ኢንዱስትሪበተለይም ከ2003ዓ.ም ወዲህ በኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች እያስፋፋ ይገኛል፡፡ በርካታ ጠቀሜታዎች…