ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ስኳር ፋብሪካ

በደቡብ ኦሞ ዞን ኛንጋቷም ወረዳ የሚካለለው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አባባ በ954 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ JJIEC በተባለ የቻይና ኩባንያ ከህዳር 2009 ዓ.ም ጀምሮ በሁለት ምዕራፍ እየተገነባ የሚገኘው ይህ ፋብሪካ፣ በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሲገባ በቀን 24 ሺ ቶን አገዳ ይፈጫል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ በፕሮጀክቱ በዋናነት የኦሞ ወንዝን መሠረት በማድረግ 100 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ሸንኮራ አገዳ ለማልማት የሚያስችል መጠነ ሰፊ የመስኖ መሰረተ ልማት ግንባታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ጊዜያዊ ግድብ/Coffer Dam ለፕሮጀክቱ ውሃ ለማቅረብ በኦሞ ወንዝ ላይ ጊዜያዊ ግድብ (ኮፈር…

ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ

በደቡብ ኦሞ ዞን በሰላማጎ ወረዳ የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አባባ 863 ኪ.ሜ ይርቃል፡፡ በስኳር ኮርፖሬሽንና በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC) መካካል ሰኔ 2004 ዓ.ም. በተፈረመ የማሻሻያ ኮንትራት መሰረት የፋብሪካው ግንባታ በ18 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ወደ ምርት እንደሚገባ ታሳቢ ተደርጎ ነበር፡፡ ይሁንና በከፍተኛ የግንባታ መጓተት ምክንያት በመንግሥት ውሳኔ ከሜቴክ ጋር የነበረው ኮንትራት በ2010 ዓ.ም. እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡ ውሉ ሲቋረጥ በስኳር ኮርፖሬሽን የውጪ አማካሪ የተረጋገጠው የፋብሪካው የግንባታ ሥራ አፈጻጸም 80% ነበር፡፡ በቀጣይ የፋብሪካው ቀሪ የግንባታ ሥራ ልምድ ባለውና በተመረጠ የውጭ ሀገር ኮንትራክተር የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡ የፋብሪካው ግንባታ ተጠናቆ በሙሉ…

ወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት

የፕሮጀክቱ ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ በ1 ሺ 30 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በትግራይ ክልል በምዕራባዊ ዞን ወልቃይት ወረዳ ይገኛል፡፡ በ40 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት ተጠቅሞ በቀን 24 ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያለው ይህ ፋብሪካ CAMC በተባለ የቻይና ኩባንያ እየተገነባ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ፋብሪካው በሁለት ምዕራፍ እየተገነባ ሲሆን፣ ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ ሲደርስ በዓመት 4 ሚሊዮን 840 ሺ ኩንታል ስኳር እና 41 ሚሊዮን 654 ሊትር ኢታኖል ያመርታል ተብሎ ታሳቢ ተደርጓል፡፡ ፕሮጀክቱ ለአገዳ ልማት የሚያስፈልገውን የመስኖ ውሃ አቅርቦት ከተከዜ፣ ከቃሌማ እና ከዛሬማ ወንዞች የሚያገኝ ይሆናል፡፡ የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ…

ጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት

ፕሮጀክቱ በአማራ ክልል አዊ ዞን ጃዊ ወረዳ ላይ የተቋቋመ ሲሆን፣ የፕሮጀክቱ ጽ/ቤትም ፋንዲቃ ከምትባለው የጃዊ ወረዳ ከተማ አጠገብ ከአዲስ አበባ በ650 ኪ.ሜ እንዲሁም ከባህር ዳር በ225 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ፕሮጀክት እያንዳንዳቸው በቀን 12 ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያላቸው ሁለት ስኳር ፋብሪካዎች በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC) ግንባታቸው ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም፣ በከፍተኛ የግንባታ መጓተት ምክንያት በስኳር ኮርፖሬሽንና በሜቴክ መካከል በ2004 ዓ.ም. ተደርሶ የነበረው የጣና በለስ ቁጥር 1 እና 2 ስኳር ፋብሪካዎች የግንባታ ውል እንደ ቅደም ተከተላቸው በ2010 ዓ.ም. እና 2009 ዓ.ም. በመንግሥት ውሳኔ እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡ የፋብሪካዎቹ ቀሪ…

ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ኢንዱስትሪ

የሀገራችን ኢንዱስትሪ በኢኮኖሚው ውስጥየመሪነቱን ሚና እንዲጫወት የላቀ አስተዋጽኦካላቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱየስኳር ልማት ፕሮጀክት ነው። ኢትዮጵያ ይህንኤክስፖርት መር የሆነ የማኑፋክቸሪንግኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማስፋፋትና ምርታማነቱንለማሳደግ የሚያስችል ከፍተኛ የሰው ኃይልናየተፈጥሮ ሃብት አላት፡፡ በተለይም ሀገሪቱ ለሸንኮራ አገዳ ልማት ተስማሚአየር ንብረት፣ በመሰኖ ሊለማ የሚችል ሰፊየእርሻ መሬት (ከ500ሺ ሄክታር በላይ) እንዲሁም በቂ ውሃ ያላት በመሆኑ ዘርፉ የበለጠትኩረት እንዲሰጠው ተደርጓል፡፡ ከዚህ ባሻገር መንግሥት የሀገሪቱ ህዝቦች ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በሚከተለው የፖሊሲአቅጣጫ መሰረት በወንጂ ሸዋና መተሓራ ስኳር ፋብሪካዎች ብቻ ለረጅም ዓመታት ያህል ተወስኖ የቆየውን የስኳር ኢንዱስትሪበተለይም ከ2003ዓ.ም ወዲህ በኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች እያስፋፋ ይገኛል፡፡ በርካታ ጠቀሜታዎች…