በስኳር ምርምርና ልማት ረቂቅ ፍኖተ-ካርታ ላይ አውደ ጥናት ተካሄደ

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ድጋፍ የሚካሄዱ ሁለት የስኳር ቴክኖሎጂ የምርምር ፕሮጀክቶችም ቀርበዋል በምርምር የተገኙ አራት ሀገር በቀል የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎችም ተመርቀዋል በስኳር ልማት ዘርፍ የተቀመጡ ግቦችን ማሳካት አላማው ያደረገ የስኳር ምርምርና ልማት ፍኖተ-ካርታ ረቂቅ ዝግጅት ላይ ግንቦት 30/2011 ዓ.ም በአዳማ ከተማ አውደ ጥናት ተካሂዷል፡፡ በስኳር ኮርፖሬሽን የምርምርና ልማት ዋና ማዕከል አዘጋጅነት በተካሄደው በዚህ አውደ ጥናት ላይ ከረቂቅ ፍኖተ ካርታው ሰነድ በተጨማሪ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የገንዘብ ድጋፍ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ የሚተገበሩ ሁለት የስኳር ቴክኖሎጂ ምርምር ፕሮጀክቶች ስራ በይፋ መጀመሩ ተበስሯል፡፡ በአውደ ጥናቱ ላይ የተገኙት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ…

የስኳር ኮርፖሬሽን ተልዕኮ፣ ራዕይ እና እሴቶች

ተልዕኮ በሀገሪቱ ያለውን እምቅ ሃብት ለማልማት የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂና የሰው ሀይል አቅም በማፍራት ስኳርና ተጓዳኝ ምርቶች በማምረትና የስኳር ተረፈ ምርትን ጥቅም ላይ በማዋል የሀገር ውስጥ ፍላጎት ከማርካትና የህዝቡን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ በተጨማሪ የጎላ የኤክስፖርት ድርሻ በመያዝ የሀገሪቱን ልማት መደገፍ፡፡ ራዕይ ቀጣይነት ባለው እድገት በ2016 ዓ.ም. በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር አምራች ሀገራት ተርታ መሰለፍ፣ እሴቶች የማያቋርጥ ለውጥና ቀጣይ ተወዳዳሪነት መልካም ሥነ ምግባር ምርታማነት የህልውናችን መሠረት ነው! ህዝባዊነት መለያችን ነው! መማር አናቋርጥም! ፈጠራንና የላቀ ሥራን እናበረታታለን! በቡድን መንፈስ መስራት መለያችን ነው! አካባቢ ጥበቃ ለልማታችን መሠረት ነው! የሰው ሃብት ልማት ለስኬታማነታችን ወሳኝ ነው!…

ፕሮጀክቶች

ኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን (ሰላማጎ እና ኛንጋቶም ወረዳዎች)፣ በቤንች ማጂ ዞን (ሱርማ እና ሜኢኒትሻሻ ወረዳዎች) እና በካፋ ዞን (ዴቻ ወረዳ) የተመረጡ አካባቢዎች እየተካሄደ የሚገኝ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡ በፕሮጀክቱ ስር እየተገነቡ ከሚገኙ አራት የስኳር ፋብሪካዎች በተሽከርካሪ ለመድረስ ከአዲስ አበባ በሆሳዕና – አርባ ምንጭ – ጂንካ መስመር ከ825-954 ኪሎ ሜትር ወይም ከአዲስ አበባ በሻሸመኔ – አርባ ምንጭ – ጂንካ መንገድ ከ859-988 ኪሎ ሜትር መጓዝን ይጠይቃል፡፡ በአየር ትራንስፖርት ከሆነ ደግሞ ከአዲስ አበባ ጂንካ ለአንድ ሰዓት ያህል በመብረር ከጂንካ ፋብሪካዎቹ ያሉበት ድረስ ከ80-220…