Opnion

በመጽሃፉ ጀርባ ላይ የሚገባ
ጎመጁ አዘውትራ ከምትናገራቸው ንግግሮች አንዱና ዋነኛው “እግዚአብሔር ለእኔ ብዙ በጎ ነገሮችን አድርጎልኛል፡፡ በጣም ይወደኛል፡፡ ከወደቅኩበት ትቢያ ላይ አንስቶኛል…” የሚለው ነው፡፡ እውነት ነው ሰው እረኛ ሲያይ እግዚአብሔር ግን ንጉስ አይቶ የለ? ” ጎመጁም ሸክም ትሆናለች ሲባል እሷ ግን ለቤተሰቦቿ፣ መስማት ለተሳናቸውና ለአካል ጉዳተኛ ወገኖቿ፣ እንዲሁም ለመላው ህዝብ ምሳሌ በመሆን ትልቅ አስተዋፅዖ በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡
ጎመጁ እስከ ዘጠኝ አመት እድሜዋ ድረስ እንደ አብዛኞቹ ልጆች የምትሰማ ከቤተሰቦቿና ከጓደኞቿ ጋር መሳቅ መጫወት የምትወድ ደስተኛ ልጅ ነበረች፡፡ ከዚያም በድንገት በማይታወቅ በሽታ በጠና ታመመችና ፈውስን ለማግኘት ከእናቷ ጋር በእጅጉ ስትንከራተት ኖረች፡፡ ይሁን እንጂ ለበሽታዋ አንዳችም መፍትሄ ሳይገኝለት የጆሮ አለመስማት ጠባሳን አስከትሎባት አለፈና ህይወቷን ለዘላለም ለወጠው፡፡ ወደ ማታውቀው የፀጥታ አለም ውስጥም ቀላቀላት፡፡
ሄለን ኬለር እንዲህ ብላለች “እኔ አይነ ስውር እንደሆንኩ ሁሉ መስማት የተሳነኝም ነኝ:: የመስማት ችግር ጥልቀት ያለውና ይበልጥ ውስብስብ ነው፡፡ ከእውርነት ያለመስማት ችግር
admin
0