• +251115526653
  • info@etsugar.com
  • Phillips Building, Chad St, Addis Ababa, Ethiopia

ስለ ግሩፑ

ተልዕኮ

  • በሀገሪቱ ያለውን እምቅ ሀብት ለማልማት የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂና የሰው ኃይል አቅም በማፍራት ስኳር፣ የስኳር ተረፈ ምርትና ተጓዳኝ ምርቶችን በማምረት  የሀገር  ውስጥ  ፍላጎት ከማርካት ባሻገር የኤክስፖርት ድርሻ በመያዝ የአገሪቱን ኢኮኖሚ መደገፍ፡፡

ራዕይ፦

  • በ2020 ዓ.ም የስኳር ፍላጎትን በሃገር ውስጥ ምርት መሸፈን ፡፡

እሴቶች

  • የዳበረ የሥራ ባህል፣
  • የላቀ ምርታማነት፣
  • ጥራት፣
  • የደንበኛ እርካታ፣
  • ትርፋማነት፣
  • ማህበራዊ ኃላፊነት፣
  • የአካባቢ ጥበቃ፣

ዓላማ

የሸንኮራ አገዳ፣ የስኳርና የስኳር ተረፈ ምርቶች መቀነስ እንዲሁም የማምረቻ ወጪ መናር መንስዔዎችን በመለየት ነባር የስኳር ፋብሪካዎችን እና አዳዲስ የስኳር ፕሮጀክቶችን ወደላቀ ምርታማነት እና ሙሉ የማምረት አቅም ማድረስ፡፡

በሚኒስቴሮች /ቤት ደንብ ቁጥር 500/2014 መሰረት የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ተግባርና ኃላፊነቶች

  •  አዋጭነታቸው የተረጋገጠ የተጀመሩና አዳዲስ የመንግሥት ስኳር ፋብሪካ ግንባታ ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም በመከታተል እና በመቆጣጠር እራሳቸውን ችለው የሚንቀሳቀሱ የስኳር ፋብሪካዎች ሆነው ሥራ እንዲጀምሩ ማድረግ፤
  • ዘመናዊና ቀልጣፋ የስርጭት ሥርዓት በመዘርጋት በአገር ውስጥ የሚመረቱም ሆነ ከውጭ ወደሀገር ውስጥ የሚገቡ ስኳር፣ የስኳር ተረፈ ምርቶችንና ተጓዳኝ የስኳር ውጤቶችን ማሰራጨት፣ እንደአስፈላጊነቱም ወደ ውጭ መላክ፤
  • የመንግሥት ስኳር ፋብሪካዎችን መደበኛና የኢንቨስትመንት ዕቅድና በጀት ማጽደቅ፣ የሥራ አፈጻጸማቸውን መገምገም፣ ቁጥጥር እና ክትትል ማድረግ፤
  • የመንግሥት ስኳር ፋብሪካዎች የንግድና የኢንቨስትመንት ሥራዎችን መደገፍ፣ እንዲሁም ከስኳር ፋብሪካዎች ጋር በመቀናጀት የስኳር ተረፈ ምርቶችንና ተጓዳኝ ውጤቶች የማምረቻ ተቋማትን መገንባት፤
  • በስኳር ኢንደስትሪ ልማት ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ አንቀጽ ፬ መሠረት የመንግሥት ስኳር ፋብሪካዎች ለመንግሥት ኢንዱስትሪ ልማት ፈንድ የሚከፍሉትን መዋጮ መጠን ለመወሰን ማስቀረት ስለሚፈቀድላቸው የስኳር ሽያጭ ገቢ መጠን አጥንቶ ለገንዘብ ሚኒስቴር ሀሳብ ማቅረብ፣ ሲፈቀድም አፈጻጸሙን መከታተል፤
  • ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር ጠንካራ ትስስር በመፍጠር በሥልጠናና በምርምር ሥራዎች የመንግሥት ስኳር ፋብሪካዎችን አቅም መገንባት የሚቻልባቸውን ሁኔታዎች ማመቻቸት፣ እንዲሁም ለመንግሥት የስኳር ፋብሪካዎች የቢዝነስ እና ሌላ የቴክኒክ ድጋፍ መሥጠት፤
  • በአገር ውስጥ ወይም በውጪ ካሉ ተቋማት ጋር በቅንጅት ወይም በተናጠል የፋብሪካ አካላትና የመለዋወጫ ዕቃዎች እንዲመረቱ መስራት እንዲሁም ስኳር ፋብሪካዎች በጋራ የሚፈልጓቸውንና በማዕቀፍ ግዥ ሊከናወኑ የሚችሉ ትላልቅ ማሽነሪዎች፣ መለዋወጫዎችና ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ከአገር ውስጥና ከውጭ በመግዛት ለፋብሪካዎች ማቅረብ፤
  • የገንዘብ ሚኒስቴር የሚሰጠውን የፖሊሲ አቅጣጫና የሚያወጣውን መመርያ መሠረት በማድረግ ቦንድ በመሸጥ ወይም ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አገር የገንዘብ ምንጮች ጋር የብድር ውል በመፈጸም ገንዘብ መሰብሰብ፤
  • የተቋቋመበትን ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ የሚያስችሉ ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን ማከናወን፡፡