• +251115526653
  • info@etsugar.com
  • Phillips Building, Chad St, Addis Ababa, Ethiopia
ዜናዎች
በፀረ-ተባይ ምርምር ላይ ያተኮረ የምክክር ወርክሾፕ ተካሄደ

በፀረ-ተባይ ምርምር ላይ ያተኮረ የምክክር ወርክሾፕ ተካሄደ

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፑ ፀድቆ ስራ በዋለው የፀረ-ተባይ ምርምር ጋይድላይን ዙሪያ ላይ ያተኮረ ወርክሾፕ ከባለድርሻ አካላት ጋር ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ናፍሌት ሆቴል ተካሄደ፡፡

በወርክሾፑ ላይ የጸረ-ተባይ ከኬሚካል አቅራቢዎች፤ ከኢትዮጵያ የግብርና ግብዓቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን፤ ከኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት፤ ከስኳር ፋብሪካዎች እና ፕሮጀክት ስራ አስኪያጆች እንዲሁም ከስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮች እና ተመራማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

የምርምርና ስልጠና ዘርፍ ም/ዋ/ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ አባይነህ ባዘዘው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የምክክር ወርክሾፑን የእለቱ የክብር እንግዳ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባ ከፍተዋል፡፡

በመድረኩም የተሻሻለው ጸረ-ተባይ መመሪያ፤ የጸረ-ተባይ ፍቃድ አሰጣጥ ሂደት እና በጸረ-ተባይ አጠቀቃም ላይ ያተኮሩ ጽሁፎች ቀርበው በዎርክሾፑ ተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት እና የተሞክሮ ልውውጥ ተደርጓል፡፡ 

የተሻሻለው የፀረ-ተባይ ምርምር ጋይድላይን (Guideline for Pesticides Testing on Sugarcane /Revised/) የምርምርና ስልጠና ዘርፍ ቺፍ አማካሪ በሆኑት በአቶ አብይ ጌታነህ የቀረበ ሲሆን ይህ መመሪያ ለረጅም አመታት እየተሰራበት ያለ መሆኑንና በተለያዩ ጊዜያት በተፈጠሩ ተቋማዊ አደረጃጀቶች እና ሌሎች ምክንያቶች ክለሳ ሲደረግበት እንደነበር ገልፀው በዚህኛው መመሪያ በተመሳሳይ ተቋሙ በአዲስ መልኩ መደራጀቱን ተከትሎ ቀደም ሲል ከኬሚካል አቅራቢዎች በተደጋጋሚ ሲነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ከግምት ለማስገባት እንደተሞከረ አብራርተዋል፡፡

የፀረ-ተባይ ሚና ለሰብል ምርታማነት ያለው አለም-አቀፋዊና ሀገራዊ ተሞክሮን በተመለከተ የዘርፉ ተመራማሪ በሆኑት በዶ/ር ሣሙኤል ተገኔ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡  

በሌላ በኩል በፀረ-ተባይ አመዘጋገብ ሂደት እና የሚታዩ ክፍተቶች ዙሪያ ከኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በተጋባዥ እንግድነት በመጡት በአቶ ፍቅረማርያም አበበ አማካይነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ቀርቧል፡፡  

የስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዋዮ ሮባ በወርክሾፑ ማጠቃለያ ንግግራቸው እንደጠቀሱት በቀጣይ ከኬሚካል አቅራቢዎች ጋር በጋራ የትብብር መንፈስ መስራት ለስኳር ኢንደስትሪውም ሆነ ለኬሚካል አቅራቢዎች የጋራ ጥቅም በመሆኑ ምርታማነትን በማሻሻል ረገድ ኬሚካል አቅራቢዎች የበኩላቸውን በማድረግ ከትርፍ ባሻገር ሃገራዊ ግዴታን መወጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም ወርክሾፑን ስፖንሰር ላደረጉ አካላት የእውቅናና ምስጋና ሰርቲፊኬት ከእለቱ የክብር እንግዳ ተበርክቷል፡፡ 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *