• +251115526653
  • info@etsugar.com
  • Phillips Building, Chad St, Addis Ababa, Ethiopia
ዜናዎች
ስኳር ፋብሪካዎች በሙሉ አቅም እንዲያመርቱ በማስቻል ላይ ያለመ ውይይት ተካሄደ

ስኳር ፋብሪካዎች በሙሉ አቅም እንዲያመርቱ በማስቻል ላይ ያለመ ውይይት ተካሄደ

በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ኦሞ ቤልት የተገነቡ ስኳር ፋብሪካዎች እየገጠሟቸው ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታትና በሙሉ አቅማቸው ማምረት እንዲችሉ ለማድረግ የክልሉ የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ከስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ጋር በጥምረት የሚሰሩበትን ሁኔታ የሚያመቻች የውይይት መድረክ በአርባምንጭ ከተማ ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በክቡር አቶ ወዮ ሮባ ከተመራው የተቋሙ አመራር አባላት በደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት በክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ ከተመራው የክልሉ ልዑክ ጋር ባደረጉት በዚሁ ውይይት በፋብሪካዎቹ የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ የሚያደርግ ስትሪንግ ኮሚቴ ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ አዋቅሮ በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

ከ65.6 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል የፈጀውንና ምንም ዓይነት መሠረተልማት ባልነበረበት የኦሞ ቤልት የተገነቡ ስኳር ፋብሪካዎች በአካባቢው የተለያዩ መሠረተልማቶች እንዲስፋፉ ያስቻሉ፤ ከክልሉ እና ከአገር ባለፈ በምስራቅ አፍሪካም ጭምር ትልቅ የልማት ተስፋ በመሆናቸው የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋረ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተመልክቷል፡፡

በዚሁ የውይይት መድረክ የተቋቋመው በየደረጃው ያለ ስትሪንግ ኮሚቴም አርብቶ አደሩን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርግ በጥናት የተደገፈ መረጃ እንዲያቀርብና ይህንኑ ተመርኩዞም የስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የበኩሉን እገዛ እንዲያደርግ እንዲሁም ፋብሪካዎቹ እየገጠሟቸው የሉት ተግዳሮቶች ሙሉ በሙሉ እንዲቀረፉ በክልሉ በኩል ትኩረት እእንደሚሰጠው ተገልፆ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *