የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ሠራተኞች በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን ሀገር አቀፍ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ አውደ ርዕይን ጎበኙ፡፡

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ሠራተኞች በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን ሀገር አቀፍ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ አውደ ርዕይን ጎበኙ፡፡
የ2016ዓ.ም የሰንደቅ ዓላማ ቀን “የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለሕብረ ብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው” በሚል መሪ ሐሳብ በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት ተከበረ፡፡
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ለሚገኙ አቅመ ደካሞች ማዕድ አጋራ፡፡የ2016 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በተከናወነ የማዕድ ማጋራት ሥነ ሥርዓት በወረዳው ለሚገኙ አቅመ ደካሞች ዱቄትና ዘይት ድጋፍ ተደርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት አመራር አባላትና ሠራተኞች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይና በአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ላይ ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አድርገዋል፡፡
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ለአካባቢው ማሕበረሰብ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸውን የመሠረት ልማት ማለትም መንገድ፣ ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ የእንስሳት ጤና ኬላዎች እንዲሁም ለእንስሳት መሻገሪያነት የሚያገለግሉ የድልድይ ግንባታዎችን አከናውኗል፡፡
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ የሁለተኛ ምዕራፍ የምርት ወቅቱን ሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም በመጀመር ስኳር እያመረተ ይገኛል፡፡
በቀን በአማካይ 3ሺህ ኩንታል ስኳር በማምረት ሂደት ላይ የሚገኘውን የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ አቅም በማሳደግ በሂደት በቀን በአማካይ እስከ 5 ሺህ ኩንታል ስኳር እንዲያመርት የሚያስችል የአገዳ አቅርቦት የማስፋፋት ሥራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ፋብሪካው እስከ መስከረም ወር 2016 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ በምርት ላይ የሚቆይ ሲሆን በዚህ የፋብሪካው የሁለተኛው ምዕራፍ የምርት ወቅትም እስከ 150 ሺህ ኩንታል ስኳር ይመረታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ፋብሪካው በመጀመሪያው ምዕራፍ የምርት ወቅት 203 ሺህ 218.5 ኩንታል ስኳር አምርቷል፡፡
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 እና ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካዎች ከሚገኙበት አካባቢ የአየር ንብረት ጋር በተያያዘ በዓመት ውስጥ ሁለት የምርት ወቅቶች አሏቸው፡፡
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የጀመራቸውን ተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎች የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ወጪ መቆጠብ እና ብክነት ማስወገድ ላይ አመራሩና ሠራተኛው ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ፡፡ የግሩፑ የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2016 ዕቅድ ላይ የዋና መስሪያ ቤት አመራር አባላትና ሠራተኞች የተሳተፉበት ውይይት በቢሾፍቱ ተደርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትና የግሩፑ የሠራተኛ ማህበር ሊቀመንበር በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክቶችና ፋብሪካ በመገኘት የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን፣ የፕሮጀክቶች የሥራ እንቅስቃሴን እና የ2016 ምርት ዘመን ዕቅድን ገመገሙ፡፡
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አመራር አባላት እና ሠራተኞች በዘንድሮው ዓመት “ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ተግባራዊ ለማድረግ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ገላን ኮንዶሚኒዬም አካባቢ በመገኘት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሄዱ፡፡
የስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ከፍተኛ አመራሮች በኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች በመገኘት የአረንጓዴ ልማት አሻራቸውን ባኖሩበት ወቅት።