• +251115526653
  • info@etsugar.com
  • Phillips Building, Chad St, Addis Ababa, Ethiopia
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ እንደ ንግድ ተቋም

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ እንደ ንግድ ተቋም

የቀድሞው ስኳር ኮርፖሬሽን በሕግ ፈርሶ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ እንደ አንድ የንግድ ተቋም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሚኒስተሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 500/2014 ሲቋቋም የስኳር ፋብሪካዎች እና ፕሮጀክቶች ላይ መሠረታዊ የአደረጃጀት ለውጥ አስከትሏል

ኢንቨስትመንት

መንግሥት የልማት ድርጅቶችን በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በርካታ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች በስኳር ኢንደስትሪ እና በተጓዳኝ ምርቶች ላይ በሽርክና (joint venture) እና በግል ኢንቨስትመንት ለመሰማራት ፍላጎታቸውን እያሳዩ ይገኛሉ፡፡ በእርግጥ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ (የቀድሞው ስኳር ኮርፖሬሽን) በዘርፉ ለመሳተፍ ፍላጎት ካላቸው ኩባንያዎች ጋር በጋራ ኢንቨስትመንት ሞዳሊቲ ለመስራት አለም አቀፍ ማስታወቂያ አውጥቶ መንቀሳቀስ የጀመረው ከመስከረም 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ነው፡፡

የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ

በሀገራችን ዘመናዊ የስኳር ኢንዱስትሪ የተጀመረው የኢትዮጵያ መንግሥት ኤች ቪ ኤ (HVA) ከተባለ የሆላንድ ኩባንያ ጋር የአክስዮን ስምምነት ከፈረመበት ከ1943ዓ.ም አንስቶ ነው፡፡ ኩባንያው 5 ሺ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ ማልሚያ መሬት ተረክቦ ሥራውን የጀመረው ከአዲስ አበባ 110 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በወንጂ ከተማ ሲሆን፣ በቅድሚያ የወንጂ ስኳር ፋብሪካን ገንብቶ መጋቢት 11 ቀን 1946ዓ.ም ስራ አስጀምሯል፡፡ ፋብሪካው በወቅቱ በቀን 1 ሺ 400…