• +251115526653
  • info@etsugar.com
  • Phillips Building, Chad St, Addis Ababa, Ethiopia
ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ

ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ

በደቡብ ኦሞ ዞን በሰላማጎ ወረዳ የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አባባ 825 ኪ.ሜ ይርቃል፡፡ ከቻይና ልማት ባንክ በተገኘ 6.67 ቢሊዮን ብር ብድር ሐምሌ 2007 ዓ.ም. ግንባታው በይፋ የተጀመረው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ መጋቢት 14/2009 ዓ.ም. የሙከራ ምርቱን ካሳካ  በኋላ ወደ መደበኛ ምርት ተሸጋግሮ በማምረት ላይ ይገኛል፡፡

መተሐራ ስኳር ፋብሪካ

መተሐራ ስኳር ፋብሪካ

ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በመቀጠል በሆላንዱ ኤች ቪ ኤ ተገንብቶ በ1962 ዓ.ም. ወደ ስራ የገባው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በ200 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ለሀገሪቱም  ከወንጂ ሸዋ በመቀጠል ሦስተኛ ስኳር ፋብሪካ ነው፡፡ ወደ 10ሺህ 230 ሄክታር በሸንኮራ አገዳ የተሸፈነ መሬት ያለው ይህ ፋብሪካ በዓመት 1.3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም አለው፡፡

ከሰም ስኳር ፋብሪካ

ከሰም ስኳር ፋብሪካ

በአፋር ክልል በዞን ሦሥት አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች በከሰም ቀበና ሸለቆ ውስጥ የሚገኘው የከሰም ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ 250 ኪ.ሜ፣ ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ደግሞ 50 ኪ.ሜ. ያህል ይርቃል፡፡

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የማስፋፊያ ፕሮጀክት አካል ሆኖ በ2003 ዓ.ም. የግንባታው ቅድመ ዝግጅት የተጀመረው የከሰም ስኳር ፋብሪካ ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ካለው ርቀትና አዋጪነት አንፃር ተጠንቶ ኋላ ላይ ራሱን ችሎ እንደ አንድ የስኳር ፋብሪካ እንዲቋቋም ተደረገ፡፡

ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ

ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ

ወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ አቅራቢያ ከአዲስ አበባ 110 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በሀገራችን የስኳር ፋብሪካ ታሪክ ፋና ወጊ የሆነው የመጀመርያ የሆነው የወንጂ ስኳር ፋብሪካ በ1946 ዓ.ም. ግንባታው ተጠናቆ ማምረት የጀመረ ሲሆን፣ የሸዋ ስኳር ፋብሪካ ደግሞ እዛው ወንጂ ላይ በ1955 ዓ.ም. ተመርቆ ስራ የጀመረ ሌላኛው ስኳር ፋብሪካ ነው፡፡ ሁለቱም ስኳር ፋብሪካዎች ኤች ቪ ኤ በተባለ የሆላንድ ኩባንያ የተገነቡና በኩባንያውና በመንግሥት የጋራ ባለቤትነት በሽርክና የተቋቋሙ ነበሩ፡፡

ጣና በለስ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ

ጣና በለስ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ

በአማራ ክልል አዊ ዞን ጃዊ ወረዳ በሚገኘው የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ሊገነቡ በዕቅድ ተይዘው ከነበሩ ሦስት ስኳር ፋብሪካዎች አንዱ የሆነው ይህ ፋብሪካ የተቋቋመው በ2003 ዓ.ም. ነው፡፡ ፋብሪካው ከአዲስ አበባ በ650 ኪ.ሜ እንዲሁም ከባህርዳር በግልገል በለስ በ225 ኪ.ሜ ርቀት አስፋልት መንገድ ላይ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ ሲታቀድ ለሶስቱም ፋብሪካዎች በ75 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ መሬት እንዲኖረው ታሳቢ ተደርጎ የተጀመረ…

ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ

ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ

የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምዕራብ 350 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በአባይ ጮመን ወረዳ በፊንጫአ ሸለቆ ውስጥ ልዩ ስሙ አገምሳ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ ይገኛል፡፡

አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ

አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ

የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ በምዕራብ ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ፣ በቡኖ በደሌና በጅማ ዞኖች በዲዴሳ ሸለቆ ውስጥ ከአዲስ አበባ-ነቀምት-በደሌ በሚወስደው መንገድ በ395 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡

ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ

ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ

የኦሞ ወንዝን በሚያዋስኑ በካፋና ቤንች ማጂ ዞኖች የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አባባ 874 ኪ.ሜ ይርቃል፡፡ ፋብሪካው ጥቅምት 4 ቀን 2011 ዓ.ም. በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ተመርቆ ሥራ ጀምሯል፡፡