በአዋሽ ተፋሰስ ዝቅተኛ አካባቢ በአፋር ክልል በሁለት ምዕራፍ በሚለማ በ50 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት የሚጠቀመው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በ670 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡

በአዋሽ ተፋሰስ ዝቅተኛ አካባቢ በአፋር ክልል በሁለት ምዕራፍ በሚለማ በ50 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት የሚጠቀመው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በ670 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
በደቡብ ኦሞ ዞን ኛንጋቷም ወረዳ የሚካለለው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አባባ በ954 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ JJIEC በተባለ የቻይና ኩባንያ ህዳር 2009 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረውና በሁለት ምዕራፍ ሊገነባ ታቅዶ ከገንዘብ አቅርቦት ጋር በተያያዘ የፋብሪካ ግንባታ ሥራው 27.7% ደርሶ የተቋረጠው
በደቡብ ኦሞ ዞን በሰላማጎ ወረዳ የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከአዲስ አባባ 863 ኪ.ሜ ይርቃል፡፡ በቀድሞው ስኳር ኮርፖሬሽንና በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC) መካካል ሰኔ 2004 ዓ.ም. በተፈረመ የማሻሻያ ኮንትራት መሰረት የፋብሪካው ግንባታ በ18 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ወደ ምርት እንደሚገባ ታሳቢ ተደርጎ ነበር፡፡
የፕሮጀክቱ ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ በ1 ሺ 30 ኪ.ሜ ርቀት ወልቃይት ወረዳ ይገኛል፡፡ፕሮጀክቱ ከእርሻ ልማቱ ጋር በተገናኘ በ40 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት ተጠቅሞ በቀን 24 ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያለው ይህ ፋብሪካ CAMC በተባለ የቻይና ኩባንያ እየተገነባ ነበር፡፡