ጎመጁ አዘውትራ ከምትናገራቸው ንግግሮች አንዱና ዋነኛው “እግዚአብሔር ለእኔ ብዙ በጎ ነገሮችን አድርጎልኛል፡፡ በጣም ይወደኛል፡፡ ከወደቅኩበት ትቢያ ላይ አንስቶኛል…” የሚለው ነው፡፡ እውነት ነው ሰው እረኛ ሲያይ እግዚአብሔር ግን ንጉስ አይቶ የለ? ” ጎመጁም ሸክም ትሆናለች ሲባል እሷ ግን ለቤተሰቦቿ፣ መስማት ለተሳናቸውና ለአካል ጉዳተኛ ወገኖቿ፣ እንዲሁም ለመላው ህዝብ ምሳሌ በመሆን ትልቅ አስተዋፅዖ በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡ ጎመጁ እስከ ዘጠኝ አመት እድሜዋ ድረስ እንደ…
