ሪፎርም እንዴት እንደሚሠራ ቋሚ ዐውደ ርዕይ የሚሆን ውጤት በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ተመለከትን። የወንጂ ስኳር ፋብሪካ የዛሬ ሰባ ዓመት ነበር በጥሩ መሠረት ላይ የተገነባው። ግን ከዘመን ጋር ካልተጓዙ መቅደም ብቻውን መብለጥን አያመጣም። ቀድሞ የበቀለን ጆሮ በኋላ የመጣ ቀንድ ሊቀድመው ይችላል። እየፈጠኑና እየፈጠሩ ዘመኑን ካልቀደሙት፣ ጊዜው ራሱ ይቀድማል። ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የዛሬ ሦስት ዓመት ለሠራተኞቹ ደሞዝ መክፈል ተስኖት ነበር። ዕዳ እንደ…