ኢንቨስትመንት
የኢንቨስትመንት ዕድሎች እና የጋራ ማልማት (joint investment) መስኮች
መንግሥት የልማት ድርጅቶችን በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በርካታ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች በስኳር ኢንደስትሪ እና በተጓዳኝ ምርቶች ላይ በሽርክና (joint venture) እና በግል ኢንቨስትመንት ለመሰማራት ፍላጎታቸውን ሲያሳዩ ቆይተዋል፡፡ በእርግጥ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ (የቀድሞው ስኳር ኮርፖሬሽን) በዘርፉ ለመሳተፍ ፍላጎት ካላቸው ኩባንያዎች ጋር በጋራ ኢንቨስትመንት ሞዳሊቲ ለመስራት አለም አቀፍ ማስታወቂያ አውጥቶ መንቀሳቀስ የጀመረው ከመስከረም 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ነው፡፡
በስኳርና በተጓዳኝ ምርቶች ላይ በጋራ ማልማት ወይም በግል ኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት የተፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎች
- የመንግሥት ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፍላጎትና የፖለቲካ ቁርጠኝነት፣
- በሀገሪቱ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ የተመቻቹ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች/Incentives ፣
- የሀገሪቱ የምጣኔ ሃብት እድገት፣
- የተትረፈረፈ የተፈጥሮ ሀብትና የሰው ኃይል፣
ኢትዮጵያ የሸንኮራ አገዳና የስኳር ተጓዳኝ ምርቶችን በስፋት ለማምረት፡–
- በመሰኖ ሊለማ የሚችልና ለአገዳ ልማት ምቹ የሆነ 4 ሚሊዮን ሄክታር ለም መሬት፣
- ተስማሚ የአየር ንብረት፣
- ለመስኖ ልማት የሚውሉ በርካታ ወንዞች፣
- ከፍተኛ የአገዳ ምርታማነት እና
- ሰፊ ቁጥር ያለው አምራች የሰው ኃይል፣
- ከሸንኮራ አገዳ ምርታማነት አኳያም ሀገሪቱ በተፈጥሮ የታደለችው የአየር ንብረትና ለም መሬት ለአገዳ ልማት ተስማሚ በመሆኑ በአማካይ በ15 ወራት በሄክታር 1 ሺ 620 ኩንታል ወይም 162 ቶን የአገዳ ምርታማነት ማግኘት የሚያስችል መሆን (ይህ አሃዝ በአለምአቀፍ የሸንኮራ አገዳ ምርታማነት ማሳያ ደረጃ መሰረት ሲሰላ በኢትዮጵያ በሄክታር በወር 108 ኩንታል አገዳ ማምረት ይቻላል፡፡ በአለምአቀፍ ደረጃ በሄክታር በተመሳሳይ ጊዜ ከሚመረተው የሸንኮራ አገዳ ምርት ጋር ሲነጻጸርም የ23 ኩንታል ብልጫ አለው)፣
- የመሠረተ ልማት አውታሮች ዝርጋታ (ትላልቅ ግድቦችና የመስኖ መሰረተ ልማት፣ መንገድ፣ የአየር ማረፊያ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ ቴሌኮሚዩኒኬሽን ወዘተ)፣
- 80 ሺ ሄክታር በአገዳ የተሸፈነ መሬት፣
- በሀገር ደረጃ ስኳር እና ኢታኖል በማምረት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ያስቆጠረ ልምድ፣
- ወደ ሥራ የገቡ 8 የስኳር ፋብሪካዎች እና ከሦስት ያላነሱ ጅምር የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች
- እያደገ የመጣ የህብረተሰቡ የስኳር ፍላጐትና ከዚህ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ሰፊ የሀገር ውስጥ ገበያ፣
- በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፉ የመጡ ስኳርን በግብዓትነት የሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች፣
- ከፍተኛ የእንስሳት ሃብት (የእንስሳት መኖ ማቀነባበርና ማድለብ ይቻላል) በዋንኛነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
የስኳር ዋንኛ ተረፈ ምርቶች (Major Sugar By-products)
- ሞላሰስ (Molasses)
- ኢታኖል (Ethanol)
- ባጋስ (Bagasse)
- ካርቦንዳይኦክሳይድ( Carbon dioxide)
የሀገራችን ተሞክሮ በስኳር ተጓዳኝ ምርቶች (Sugar Co-products)
- የኤሌክትሪክ ኃይል (Electricity)
- ፍራፍሬ (Fruits) ; Orange, Banana, Mango
- የእንስሳት መኖ (Animal feed)
- ከብት ማድለብ (Cattle Fattening)
- ጥጥ (Cotton)
- ሩዝ (Rice)
- አኩሪ አተር (Soya bean)
- ሰሊጥ (Sesame)
- ስንዴ (Wheat)
- ቦሎቄ (Haricot bean)
- ማሾ (Mung bean)
በሽርክና (Joint venture) ወይም በግል ኢንቨስት የሚደረግባቸው መስኮች
- የስኳር ፕሮጀክቶች ግንባታ፣
- ስኳር ፋብሪካ የማስተዳደርና ኦፕሬሽን የመምራት ሥራ፣
- የኢታኖል ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ የማስተዳደርና ኦፕሬሽን የመምራት ሥራ፣
- የተለያዩ የስኳር ተጓዳኝ ምርቶች ልማት፣
- የመስኖ ዝርጋታ፣ የመሬት ዝግጅት እና ሸንኮራ አገዳ ልማት ፕሮጀክቶች፣
- የስኳር ፋብሪካ የመለዋወጫ እቃዎች ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣
- የእንስሳት መኖ ልማትና ማድለብ ሥራ፣
- የወረቀት ማምረቻ ፋብሪካ፣
- የችፕቦርድ ማምረቻ ፋብሪካ፣
- የአልክሆል መጠጥ ኢንዱስትሪ፣
- የስኳር ማሸጊያ ከረጢት/ጆንያ ማምረቻ ፋብሪካ፣
- የቀለም ማምረቻ ፋብሪካ ወዘተ
የመንግስትና የግል ሽርክና
ኔክሰስ ማኑፋክቸሪንግ አክሲዮን ኩባንያ
ኔክሰስ ማኑፋክቸሪንግ አክሲየን ኩባንያ የስኳር ተረፈ ምርት የሆነውን ሞላሰስን በመጠቀም የተለያዩ የአልኮል ዓይነቶችን የሚያመርት የግል ኩባንያ ነው፡፡ ኩባንያው በአሁኑ ጊዜ በቀን 50 ሺ ሊትር አልኮል የማምረት አቅም ያለው ሲሆን ይህ አቅሙ በቀጣይ ወደ 100 ሺህ ሊትር ሊያድግ የሚችል ነው፡፡
ኔክሰስ ማኑፋክቸሪንግ አክሲየን ኩባንያ ከቀድሞው ስኳር ኮርፖሬሽን ጋር በሚያዚያ ወር 2010 ዓ.ም በተፈራረመው ስምምነት መሠረት የሞላሰስ ማጣሪያ ፋብሪካ በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ አቅራቢያ በመገንባት በ2014ዓ.ም ኤታኖል ማምረት ጀምሯል፡፡
ፋብሪካው በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች መካከል በተደረገው ስምምነት መሠረት ለኤታኖል ምርቱ ዋንኛ ግብዓት የሆነውን ሞላሰስ እና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶችን ማለትም ንጹህ ውኃ፣ ስቲም እና የመሳሰሉትን ከኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ በክፍያ በማግኘት ሥራውን በማከናወን ላይ የሚገኝ ኩባንያ ነው፡፡
ሮራንክ ንግድ አክሲዮን ኩባንያ
ሮራንክ ንግድ አክሲዮን ኩባንያ የአልኮል መጠጦችን በማምረት ላይ የተሰማራ የግል ኩባንያ ነው፡፡ ኩባንያው ከቀድሞው ስኳር ኮርፖሬሽን ጋር በመጋቢት ወር 2009 ዓ.ም በተፈራረመው ስምምነት መሠረት የሞላሰስ ማጣሪያ ፋብሪካ በከሰም ስኳር ፋብሪካ በመገንባት በ2015ዓ.ም ኤታኖል ለማምረት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
ኩባንያው የስኳር ተረፈ ምርት የሆነውን ሞላሰስን በመጠቀም የተለያዩ የአልኮል ዓይነቶችን የሚያመርት ሲሆን ኩባንያው በአሁኑ ጊዜ በቀን 50 ሺ ሊትር አልኮል የማምረት አቅም ያለውና ይህ አቅሙም በቀጣይ በቀን ወደ 100 ሺህ ሊትር ሊያድግ የሚችል ነው፡፡
የሮራንክ ንግድ አክሲየን ኩባንያ የኤታኖል ፋብሪካ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሚገኘው ከሰም ስኳር ፋብሪካ ግቢ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ፋብሪካው በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች መካከል በሚደረስ የዋጋ ስምምነት መሠረት ለኤታኖል ምርቱ ዋንኛ ግብዓት የሆነውን ሞላሰስ እና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶችን ማለትም ንጹህ ውኃ፣ ስቲም እና የመሳሰሉትን ከከሰም ስኳር ፋብሪካ በክፍያ የሚያገኝ ነው፡፡