ዜናዎች

ፋብሪካው ለማራ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ለማራ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ብር 130,000 (አንድ መቶ ሠላሣ ሺህ ብር) የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ.ም ድጋፍ አደረገ፡፡
ፋብሪካው ያደረገው የደብተር፣ እስክርቢቶ፣ ወረቀት፣ ጠመኔ እና የማስመሪያ ድጋፍ ቀጣይነት የሚኖረው መሆኑን የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ፈለቀ ቶማ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅትም ፋብሪካው የሚያደርገው ድጋፍ ቀጣይነት ያለው መሆኑን በመግለጽ ለመማር ማስተማሩ ፕሮግራም ውጤታማነት የሚመለከታቸው የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
ፋብሪካው የሠራተኞቹን ቤተሰቦች በትምህርት ገበታ ላይ እንዲገኙ እና የአካባቢው አርብቶ አደር ልጆችም ለመጀመሪያ ጊዜ የመማር ዕድል እንዲያገኙ በ2014 ዓ.ም ከሣላማጎ ወረዳ ጋር በመቀናጀት እና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን በማሟላት የመማር ማስተማር ፕሮግራም ማስጀመሩ የሚታወስ ሲሆን ጥቂት ቁጥር ባላቸው የአካባቢው አርብቶ አደር ልጆች የተጀመረው የትምህርት ሂደት በየዓመቱ እያደገ መጥቶ በ2018 ዓ.ም ከ1ኛ-5ኛ ክፍል በአጠቃላይ 312 ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡

admin
0