• +251115526653
  • info@etsugar.com
  • Phillips Building, Chad St, Addis Ababa, Ethiopia
በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ተቀጥረው ከሚሰሩ የሱርማ ማሕበረሰብ አባላት ጋር ውይይት ተካሄደ

በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ተቀጥረው ከሚሰሩ የሱርማ ማሕበረሰብ አባላት ጋር ውይይት ተካሄደ

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ተቀጥረው በመስራት ላይ ከሚገኙ የሱርማ ማሕበረሰብ አባላት ጋር ጥቅምት 19 ቀን 2017ዓ.ም የአካባቢውን ጸጥታና ደህንነት በተመለከተ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ ላይ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1/3 ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ካሳ ተስፋዬ፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት እና ፌደራል ፖሊስ አመራር አካላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ ባደረጉት ንግግር…

በ2017 የመጀመሪያ 100 ቀናት የመንግስት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ

በ2017 የመጀመሪያ 100 ቀናት የመንግስት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በያዝነው በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት የመንግስት የዕቅድ አፈጻጸም ላይ ጥቅምት 20 ቀን 2017ዓ.ም በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጁስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱ የተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት የመንግስትን የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የግሩፑ የማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታፈሰ አሰፋ እንደ አገር የተካሄዱ የሪፎርም ሥራዎች ያስገኟቸውን ውጤቶችና…

ፋብሪካው ከአካባቢው አርብቶ አደር ማህበረሰብ ጋር ውይይት አደረገ

ፋብሪካው ከአካባቢው አርብቶ አደር ማህበረሰብ ጋር ውይይት አደረገ

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1/3 ስኳር ፋብሪካ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ልማት ፕሮጀክት በሚገኝበት አካባቢ ነዋሪ ከሆኑ የቦዲ ማህረሰብ አባላት ጋር ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ጸጥታ እና ደህንነነትን እንዲሁም የሸንኮራ አገዳ ልማት ሥራውን በተመለከተ ውይይት አደረገ፡፡ በውይይቱ የማህበረሰቡ ባላባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የመስተዳደር አካላት እንዲሁም በፋብሪካው በቋሚነትና በጊዜያዊነት በመስራት ላይ የሚገኙ የማህበረሰቡ ተወላጅ የደህንነትና ጥበቃ፣ የጋራዥ ሠራተኞች እና ኦፕሬተሮች ተሳታፊ…

ፋብሪካው ከጸጥታ አካላት ጥምር ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት አካሄደ

ፋብሪካው ከጸጥታ አካላት ጥምር ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት አካሄደ

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3/1 ስኳር ፋብሪካ የአካባቢውን ሰላምና ደሕንነት በማስጠበቅ የምርት ሥራዎችን ያለዕክል ማከናወን ይችል ዘንድ ከጸጥታ አካላት ጥምር ኮሚቴ አባላት ጋር ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ውይይት አካሄደ ፡፡ የውይይት መድረኩን የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ካሳ ተስፋዬ እና የጸጥታ አካለቱ የሥራ ኃላፊዎች በጋራ የመሩት ሲሆን ከፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች የተዋቀረ…

ለኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

ለኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

ከፋብሪካው ፎርማኖች፣ ሱፐርቫይዘሮች እና ሲኒየር ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተደርጓል የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለዋና መስሪያ ቤት እና ፋብሪካዎች አመራሮችና ሠራተኞች በተከታታይ በመስጠት ላይ የሚገኘው የአቅም ግንባታ ስልጠና ለኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም በፋብሪካው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተሰጥቷል፡፡ በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር…

የግሩፑ የምርምርና ስልጠና ዘርፍ አመታዊ የምርምር ሥራዎች ግምገማ ተጠናቀቀ

የግሩፑ የምርምርና ስልጠና ዘርፍ አመታዊ የምርምር ሥራዎች ግምገማ ተጠናቀቀ

በሃገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 28 እስከ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ለ3 ተከተታይ ቀናት ወንጂ በሚገኘው የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የምርምርና ስልጠና ዘርፍ የስኳር አካዳሚ ሲካሄድ የቆየው አመታዊ የምርምር ሥራዎች ግምገማ (National Research Review) በዛሬው ዕለት ተጠናቋል፡፡ በመድረኩም 7 የተጠናቀቁ የምርምር ውጤቶች እና 11 አዳዲስ የምርምር ፕሮፖዛሎች በአግሮኖሚ፣ በሰብል ጥበቃ፣ በዝርያ ማሻሻያ፣ በአፈር ሣይንስ፣ በመስኖ ምህንድስና እና በስኳር ቴክኖሎጂ የምርምር መስኮች…

በአመራር ክህሎት ላይ ያተኮረ ስልጠና በስኳር አካዳሚው እየተሰጠ ነው

በአመራር ክህሎት ላይ ያተኮረ ስልጠና በስኳር አካዳሚው እየተሰጠ ነው

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ በአዲስ ተልዕኮ ከመቋቋሙ ጋር ተያይዞ እራሳቸውን ችለው እንዲቋቋሙ ከተደረጉ ሶስት ስኳር ፋብሪካዎች ለተውጣጡ 36 ቡድን መሪዎች እና ሱፕርቫይዘሮች ከመስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በአመራር ክህሎት ዙሪያ ያጠነጠነ ስልጠና በግሩፑ የስኳር አካዳሚ እየተሰጠ ነው፡፡ በዚህ የስልጠና መርሐግብር ከፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ 18፤ ከመተሀራ ስኳር ፋብሪካ 10 እንዲሁም ከወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ 8 አመራሮች እየተሳተፉ የሚገኙ ሲሆን በዚህም የሶስቱ…

“የአገር ሀብት የሆነውን ፋብሪካ ውጤታማ ለማድረግ የጸጥታ አካላት በቅንጅት መስራት ይጠበቅባቸዋል”

“የአገር ሀብት የሆነውን ፋብሪካ ውጤታማ ለማድረግ የጸጥታ አካላት በቅንጅት መስራት ይጠበቅባቸዋል”

                             የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባ ከፎርማኖች፣ሱፐርቫይዘሮች እና ሲኒየር ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተካሄደ ከፍተኛ መዕለ ንዋይ የፈሰሰበትንና የአገር ሀብት የሆነውን የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 እና 1 ስኳር ፋብሪካ የሚጠበቅበትን ምርት በተገቢው መልኩ እንዲያመርትና ውጤታማ እንዲሆን በአካባቢው ተሰማርተው የሚገኙ የጸጥታ እና የአስተዳደር አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባ…

ሠራተኛው የፋብሪካው ባለቤት ሆኖ መስራት እንደሚጠበቅበት ተገለጸ

ሠራተኛው የፋብሪካው ባለቤት ሆኖ መስራት እንደሚጠበቅበት ተገለጸ

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 እና 1 ስኳር ፋብሪካ አመራሮችና ሠራተኞች የስኳር ምርትን ለማሳደግ፣ የማምረቻ ወጪዎችን ለመቀነስና በዋናነት ብክነትን ለማስወገድ በባለቤትነት መንፈስ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባ ግሩፑ ለኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 እና 1 ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ያዘጋጀውን የአቅም ግንባታ ስልጠና በንግግር በከፈቱበት ወቅት እንዳሉት የፋብሪካው የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች የስኳር ምርትን ለማሳደግ፣…

ለኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች የሥራ መሪዎች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ

ለኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች የሥራ መሪዎች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች የሥራ መሪዎች ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ ከመስከረም 23 እስከ መስከረም 26 ቀን 2017ዓ.ም በዘለቀው በዚህ የሥራ መሪዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና የለውጥ ዕድሎችና ፈተናዎች እንዲሁም ስጋቶች፣ የለውጥ ዕድሎችን የመጠቀም ብቃት መገንባት፡- የአመራር ምንነት፣ ዕድገት ባሕሪያትና ተግዳሮቶች፣ የቡድን መንፈስ ግንባታ አስፈላጊነት፣ ስልቶችና ፈተናዎች፤ አሠራሮችን የበለጠ ሳይናሳዊ ማድረግ፡- የተቋም ሥራ አፈጻጸምን ማዘመንና ማሻሻል፣…