• +251115526653
  • info@etsugar.com
  • Phillips Building, Chad St, Addis Ababa, Ethiopia
Uncategorized
በ2017 የመጀመሪያ 100 ቀናት የመንግስት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ

በ2017 የመጀመሪያ 100 ቀናት የመንግስት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በያዝነው በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት የመንግስት የዕቅድ አፈጻጸም ላይ ጥቅምት 20 ቀን 2017ዓ.ም በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጁስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱ የተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት የመንግስትን የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የግሩፑ የማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታፈሰ አሰፋ እንደ አገር የተካሄዱ የሪፎርም ሥራዎች ያስገኟቸውን ውጤቶችና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ምን እንደሚመስሉ በወቅቱ ዘርዝረዋል፡፡

በገለጻቸውም ዓለም ዓቀፍ የፖለቲካና የኢኮኖሚ አዝማሚያዎች ምን እንደሚመስሉ፣ የሚጠበቁ ሁኔታዎች ምን እንደሆኑ፣ አገሪቱ ያደረገችው የኢኮኖሚ ሪፎርም አፈጻጸም ምን እንደሚመስል እንዲሁም የስኳር ልማት ዘርፉን ጨምሮ እንደ አገር የዋና ዋና ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አስረድተው በስብሰባው ተሳታፊዎች በኩል ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

አገሪቱ በልዩ ልዩ የምጣኔ ሀብት መለኪያዎች መልካም ውጤቶችን ማስመዝገቧን የተናገሩት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው የግሩፑ ሠራተኞችና የሥራ መሪዎች በአገር ደረጃ የተመዘገበው ውጤት ቀጣይ እንዲሆን በተሰማሩበት የስኳር ልማት ዘርፍ የበኩላቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡