ትናንት የተጀመረውና ለኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች የሥራ መሪዎች በመሰጠት ላይ የሚገኘው የአቅም ግንባታ ስልጠና ዛሬም ቀጥሏል፡፡ በዛሬው የጠዋት መርሐ ግብር “የለውጥ ዕድሎችን የመጠቀም ብቃት፡- የአመራር ምንነት፣ ዕድገት፣ ባሕሪያትና ተግዳሮቶች” በሚል ርዕስ የመነሻ ሐሳብ የግሩፑ የኮርፖሬት ጉዳዮች ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት በአቶ ዘመድኩን ተክሌ ቀርቧል፡፡ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው የአመራር ብቃት ፣ የእውነተኛ መሪ መርሆዎች፣ መሪዎች የሚያነሷቸው ጥያቄዎች፣ የመሪና የተከታይ…