• +251115526653
  • info@etsugar.com
  • Phillips Building, Chad St, Addis Ababa, Ethiopia
ዜናዎች
ፋብሪካው ከጸጥታ አካላት ጥምር ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት አካሄደ

ፋብሪካው ከጸጥታ አካላት ጥምር ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት አካሄደ

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3/1 ስኳር ፋብሪካ የአካባቢውን ሰላምና ደሕንነት በማስጠበቅ የምርት ሥራዎችን ያለዕክል ማከናወን ይችል ዘንድ ከጸጥታ አካላት ጥምር ኮሚቴ አባላት ጋር ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ውይይት አካሄደ ፡፡

የውይይት መድረኩን የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ካሳ ተስፋዬ እና የጸጥታ አካለቱ የሥራ ኃላፊዎች በጋራ የመሩት ሲሆን ከፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች የተዋቀረ ኮሚቴ ያዘጋጀው የውይይት መነሻ ሰነድ ነው ቀርቦ ውይይት የተካሄደው፡፡

በውይይቱም የፋብሪካው ማኔጅመንት አካላት፣ የሐገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ሥራ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን በፋብሪካው የምርት ሂደት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይፈጥራሉ ተብለው በሚታሰቡ የተለያዩ ችግሮች ዙሪያ በጥልቀትና በስፋት ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱ ማጠቃለያም  ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በየደረጃው መፍታት እንዲቻል የአሰራር አቅጣጫ በማስቀመጥና የዝግጅት ሥራዎችን በማከናወን ወደ ስራ መግባት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማካሄዳቸውን የፋብሪካው ዘገባ አመልክቷል፡፡