በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዲስ ለተቋቋመው የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ስለኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ዘርፍ የማስተዋወቂያ መድረክ ሚያዚያ 1 ቀን 2015 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዷል፡፡
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዲስ ለተቋቋመው የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ስለኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ዘርፍ የማስተዋወቂያ መድረክ ሚያዚያ 1 ቀን 2015 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዷል፡፡
የቀድሞው ስኳር ኮርፖሬሽን በሕግ ፈርሶ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ እንደ አንድ የንግድ ተቋም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሚኒስተሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 500/2014 ሲቋቋም የስኳር ፋብሪካዎች እና ፕሮጀክቶች ላይ መሠረታዊ የአደረጃጀት ለውጥ አስከትሏል
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ሠራተኛ በአገሪቱ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶችን በሚገባ ተገንዝቦ ስኬቶቹን የበለጠ ለማጎልበት የማይተካ ሚና እንዳለው ተገለጸ፡፡
በአዋሽ ተፋሰስ ዝቅተኛ አካባቢ በአፋር ክልል በሁለት ምዕራፍ በሚለማ በ50 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት የሚጠቀመው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በ670 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
በደቡብ ኦሞ ዞን በሰላማጎ ወረዳ የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አባባ 825 ኪ.ሜ ይርቃል፡፡ ከቻይና ልማት ባንክ በተገኘ 6.67 ቢሊዮን ብር ብድር ሐምሌ 2007 ዓ.ም. ግንባታው በይፋ የተጀመረው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ መጋቢት 14/2009 ዓ.ም. የሙከራ ምርቱን ካሳካ በኋላ ወደ መደበኛ ምርት ተሸጋግሮ በማምረት ላይ ይገኛል፡፡
መንግሥት የልማት ድርጅቶችን በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በርካታ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች በስኳር ኢንደስትሪ እና በተጓዳኝ ምርቶች ላይ በሽርክና (joint venture) እና በግል ኢንቨስትመንት ለመሰማራት ፍላጎታቸውን እያሳዩ ይገኛሉ፡፡ በእርግጥ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ (የቀድሞው ስኳር ኮርፖሬሽን) በዘርፉ ለመሳተፍ ፍላጎት ካላቸው ኩባንያዎች ጋር በጋራ ኢንቨስትመንት ሞዳሊቲ ለመስራት አለም አቀፍ ማስታወቂያ አውጥቶ መንቀሳቀስ የጀመረው ከመስከረም 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ነው፡፡
ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በመቀጠል በሆላንዱ ኤች ቪ ኤ ተገንብቶ በ1962 ዓ.ም. ወደ ስራ የገባው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በ200 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ለሀገሪቱም ከወንጂ ሸዋ በመቀጠል ሦስተኛ ስኳር ፋብሪካ ነው፡፡ ወደ 10ሺህ 230 ሄክታር በሸንኮራ አገዳ የተሸፈነ መሬት ያለው ይህ ፋብሪካ በዓመት 1.3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም አለው፡፡
በሀገራችን በስኳር ኢንዱስትሪ የምርምር ሥራ የተጀመረው ኤች.ቪ.ኤ በተባለ የሆላንድ ኩባንያ እ.ኤ.አ. በ1951 ነበር። የምርምር ክፍሉ ዋናው ማዕከል በአምስተርዳም ሆኖ በወቅቱ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የስኳር ፋብሪካዎች ጠንካራ ድጋፍ ይሰጥ ነበር፡፡ ኩባንያው በወንጂ ሸንኮራ አገዳ መትከልና ስኳር ማምረት ሲጀምር እ.ኤ.አ. ከ1958 አንስቶ በስኳር ኢንዱስትሪ ሥልጠና ይሰጥ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ኋላ ላይ የፋብሪካዎቹን ወደ መንግሥት ይዞታነት መሸጋገር ተከትሎ የምርምር ሥራው በተለያዩ አደረጃጀቶች ሲመራ ቆይቶ…
በደቡብ ኦሞ ዞን ኛንጋቷም ወረዳ የሚካለለው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አባባ በ954 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ JJIEC በተባለ የቻይና ኩባንያ ህዳር 2009 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረውና በሁለት ምዕራፍ ሊገነባ ታቅዶ ከገንዘብ አቅርቦት ጋር በተያያዘ የፋብሪካ ግንባታ ሥራው 27.7% ደርሶ የተቋረጠው
በደቡብ ኦሞ ዞን በሰላማጎ ወረዳ የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ልማት ፕሮጀክት ከአዲስ አባባ 863 ኪ.ሜ ይርቃል፡፡ በቀድሞው ስኳር ኮርፖሬሽንና በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC) መካካል ሰኔ 2004 ዓ.ም. በተፈረመ የማሻሻያ ኮንትራት መሰረት የፋብሪካው ግንባታ በ18 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ወደ ምርት እንደሚገባ ታሳቢ ተደርጎ ነበር፡፡