• +251115526653
  • info@etsugar.com
  • Phillips Building, Chad St, Addis Ababa, Ethiopia
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ከሐምሌ ወር ጀምሮ ስኳር እያመረተ ይገኛል

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ከሐምሌ ወር ጀምሮ ስኳር እያመረተ ይገኛል

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ የሁለተኛ ምዕራፍ የምርት ወቅቱን ሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም በመጀመር ስኳር እያመረተ ይገኛል፡፡
በቀን በአማካይ 3ሺህ ኩንታል ስኳር በማምረት ሂደት ላይ የሚገኘውን የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ አቅም በማሳደግ በሂደት በቀን በአማካይ እስከ 5 ሺህ ኩንታል ስኳር እንዲያመርት የሚያስችል የአገዳ አቅርቦት የማስፋፋት ሥራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ፋብሪካው እስከ መስከረም ወር 2016 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ በምርት ላይ የሚቆይ ሲሆን በዚህ የፋብሪካው የሁለተኛው ምዕራፍ የምርት ወቅትም እስከ 150 ሺህ ኩንታል ስኳር ይመረታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 
ፋብሪካው በመጀመሪያው ምዕራፍ የምርት ወቅት 203 ሺህ 218.5 ኩንታል ስኳር አምርቷል፡፡
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 እና ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካዎች ከሚገኙበት አካባቢ የአየር ንብረት ጋር በተያያዘ በዓመት ውስጥ ሁለት የምርት ወቅቶች አሏቸው፡፡

የተቋሙን ሪፎርም የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ወጪ መቆጠብና ብክነትን ማስወገድ እንደሚገባ ተገለጸ

የተቋሙን ሪፎርም የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ወጪ መቆጠብና ብክነትን ማስወገድ እንደሚገባ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የጀመራቸውን ተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎች የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ወጪ መቆጠብ እና ብክነት ማስወገድ ላይ አመራሩና ሠራተኛው ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ፡፡ የግሩፑ የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2016 ዕቅድ ላይ የዋና መስሪያ ቤት አመራር አባላትና ሠራተኞች የተሳተፉበት ውይይት በቢሾፍቱ ተደርጓል፡፡

የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክቶችና ፋብሪካ የ2015 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸምና የ2016 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ግምገማ ተካሄደ

የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክቶችና ፋብሪካ የ2015 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸምና የ2016 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ግምገማ ተካሄደ

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትና የግሩፑ የሠራተኛ ማህበር ሊቀመንበር በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክቶችና ፋብሪካ በመገኘት የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን፣ የፕሮጀክቶች የሥራ እንቅስቃሴን እና የ2016 ምርት ዘመን ዕቅድን ገመገሙ፡፡

የስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አመራር አባላትና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም አከናወኑ

የስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አመራር አባላትና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም አከናወኑ

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አመራር አባላት እና ሠራተኞች በዘንድሮው ዓመት “ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ተግባራዊ ለማድረግ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ገላን ኮንዶሚኒዬም አካባቢ በመገኘት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሄዱ፡፡

የዋና መስሪያ ቤት አድራሻ ለውጥ ማስታወቂያ

የዋና መስሪያ ቤት አድራሻ ለውጥ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ ቀድሞ ከነበረበት ሕንፃ ሜክሲኮ አደባባይ ወደሚገኘው ፊሊፕስ ሕንፃ የተዛወረ መሆኑን ለክቡራን ደንበኞቹ እና ለባለድርሻ አካላት እያስታወቀ የግሩፑ የግብይት ዘርፍ ግን ለጊዜው በነበረበት ሕንፃ የሚቆይ መሆኑን ይገልጻል፡፡

በጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት አይ.ኤስ.ኦ 9001 2015 ላይ የተኮረ ሥልጠና እየተሰጠ ነው

በጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት አይ.ኤስ.ኦ 9001 2015 ላይ የተኮረ ሥልጠና እየተሰጠ ነው

በጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት አይ.ኤስ.ኦ 9001 2015 ላይ ያተኮረ የሁለት ቀናት ሥልጠና ለኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ እና ለስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ከፍተኛ አመራር አባላት ከዛሬ ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በግሩፑ ዋና መስሪያ ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በመሰጠት ላይ ነው፡፡

ግሩፑ በዓለም ዓቀፍ ግልግል ፍርድ ቤት ተፈረደለት

ግሩፑ በዓለም ዓቀፍ ግልግል ፍርድ ቤት ተፈረደለት

የቀድሞው ስኳር ኮርፖሬሽን ከቻይናው ዘይጂያንግ ቲምስ ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚክ ኮኦፕሬሽን ሊሚትድ (ZHEIJIANG TEAMS INTERNATIONAL ECONOMIC LTD) ከተሰኘው ኩባንያ ጋር የግብርና ማሽነሪዎችን ግዥ ለመፈጸም በገባው ውል መሠረት ስላልቀረበለት በዓለም ዓቀፍ ንግድ ምክር ቤት ሲያደርግ በነበረው ክርክር ተፈረደለት፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ከሠራተኛውና ከተቋሙ ማኔጅመንት ጋር ተወያየ

ቋሚ ኮሚቴው ከሠራተኛውና ከተቋሙ ማኔጅመንት ጋር ተወያየ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ሠራተኞችና ከተቋሙ ከፍተኛ አመራር ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው ቃሊቲ የሚገኘውን የስኳር ማዕከላዊ መጋዘንና በግንባታ ላይ የሚገኘውን የግሩፑን የወደፊት ዋና መስሪያ ቤት የሕንጻ ግንባታ ሂደትን ጎብኝቷል፡፡