• +251115526653
  • info@etsugar.com
  • Phillips Building, Chad St, Addis Ababa, Ethiopia
ዜናዎች
የተቋሙን ሪፎርም የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ወጪ መቆጠብና ብክነትን ማስወገድ እንደሚገባ ተገለጸ

የተቋሙን ሪፎርም የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ወጪ መቆጠብና ብክነትን ማስወገድ እንደሚገባ ተገለጸ

  • በግሩፑ የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2016 ዕቅድ ላይ ውይይት ተደርጓል

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የጀመራቸውን ተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎች የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ወጪ መቆጠብ እና ብክነት ማስወገድ ላይ አመራሩና ሠራተኛው ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ፡፡ የግሩፑ የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2016 ዕቅድ ላይ የዋና መስሪያ ቤት አመራር አባላትና ሠራተኞች የተሳተፉበት ውይይት በቢሾፍቱ ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2016 ዕቅድ ግምገማ መድረክ መክፈቻ ላይ የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባ ባደረጉት ንግግር የተቋሙ የሪፎርም ሥራ ካሉት ሁለት ምዕራፎች መካከል ወጪ መቀነስና ብክነትን ማስወገድ የመጀመሪያው በመሆኑ በዚህ ረገድ አሁን የተመዘገበውን አበረታች ውጤት ለማስቀጠል፣ የበለጠ ውጤታማ እና ተቋማዊ ባህል ለማድረግ አመራሩና ሠራተኛው ርብርብ ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

የግሩፑ የሪፎርም ሥራ ዋና ዓላማ ኢንዱስትሪውን ካለበት አስቸጋሪ ሁኔታ አውጥቶ ወደቀደመ ምርታማነቱ መመለስ መሆኑን የገለጹት ክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚው ወጪ በመቀነስ ረገድ በተከናወኑ ተግባራት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተቋሙ የሚያበረታታ ርቀት መጓዝ መቻሉን አመልክተዋል፡፡ ለአብነትም የዋና መስሪያ ቤት ቢሮን በመቀየር ለኪራይ ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ ወጪ ማዳን መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

የሪፎርሙ ሁለተኛ ዓላማ ፋብሪካዎችን ወደቀደመ ምርታማነታቸው ለመመለስ በእርሻና በፋብሪካ ዘርፍ እንዲሁም በመሠረተ ልማት አቅርቦት ረገድ ያልተሰሩ ቀሪ ሥራዎችን በ2016 በጀት አመት መስራት እና በ2017ዓ.ም ተቋሙን ካሉበት ተግዳሮቶች አላቆ ቀና ማድረግ መሆኑንና ለዚህም ሰፊ ርብርብ እንደሚደረግ ዋና ሥራ አስፈጻሚው በመክፈቻ ንግግራቸው፡፡

የግሩፑ የ2015 ዕቅድ አፈጻጸምና የ2016 በጀት ዕቅድ በዕቅድ፣ ልማትና ሥጋት አስተዳደር መምሪያ ሥራ አስኪያጅ በአቶ ዮሴፍ በጋሻው ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በውይይቱም ግሩፑ ባከናወናቸው የሪፎርም ሥራዎች አበረታች ለውጦች መታየት መጀመራቸውን አስተያየት ሰጪዎች አንስተዋል፡፡ ከነዚህም መካከል በወጪ ቅነሳ ረገድ የተከናወነው ተግባር የሚያስመሰግንና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው ተግባር መሆን አለበትም ብለዋል፡፡

በግብአት አቅርቦት፣ በቴክኒክ ክፍተት እና በመሠረተ ልማት አለመሟላት ረገድ ያሉ ክፍተቶችን በማስተካከል ተቋሙን ቀድሞ ወደነበረበት ምርታማነት ለመመለስ ርብርብ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑም በአስተያየት ሰጪዎች ተጠቁሟል፡፡

ከውይይቱ በኋላ ማጠቃለያ የሰጡት የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባ የ2016 በጀት አመት ለግሩፑ በጣም ወሳኝ አመት በመሆኑ ሁሉም ርብርብ ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡

ይህ አዲሱ በጀት ዓመት በግብአት አቅርቦት፣ በወጪ ቅነሳ፣ በንብረት አያያዝ፣ በኦፕሬሽንና ፕሮጀክት እና በሌሎችም መስኮች በርካታ ተግባራትን ማከናወን የሚጠበቅብን ዓመት በመሆኑ አመራሩና ሠራተኛው ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጎ ወደስራ መግባት የሚጠበቅበት መሆኑን አሳስበዋል፡፡

መንግስት ለስኳር ኢንዱስትሪው የተለየ ትኩረት መስጠቱን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው የግሩፑ ማኔጅመንትም በ2015 ፈታኝ የነበሩ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ኃላፊነት ወስዶ ሥራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *