በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3/1 ስኳር ፋብሪካ የአካባቢውን ሰላምና ደሕንነት በማስጠበቅ የምርት ሥራዎችን ያለዕክል ማከናወን ይችል ዘንድ ከጸጥታ አካላት ጥምር ኮሚቴ አባላት ጋር ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ውይይት አካሄደ ፡፡ የውይይት መድረኩን የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ካሳ ተስፋዬ እና የጸጥታ አካለቱ የሥራ ኃላፊዎች በጋራ የመሩት ሲሆን ከፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች የተዋቀረ…