• +251115526653
  • info@etsugar.com
  • Phillips Building, Chad St, Addis Ababa, Ethiopia
የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ

ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የጨረታ ቁጥር LP/OT/03/SIG/2019 የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ፊሊፕስ ህንፃ ላይ ለዋና መስሪያ ቤት አገልግሎት የሚጠቀምበትን ቢሮ ለ2019 ዓ.ም የፅዳት አገልግሎት ግዥ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ ለ2018/19 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት/ የታክስ ክሊራንስ…

በአምባሳደር ግርማ ብሩ ሰብሳቢነት የሚመራው የግሩፑ የሥራ አመራር ቦርድ የዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ ግንባታን ጎበኘ

በአምባሳደር ግርማ ብሩ ሰብሳቢነት የሚመራው የግሩፑ የሥራ አመራር ቦርድ የዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ ግንባታን ጎበኘ

በክቡር አምባሳደር ግርማ ብሩ የሚመራው የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሥራ አመራር ቦርድ የግሩፑን የወደፊት የዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ የግንባታ ሂደትን ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጎብኝቷል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት የህንጻ ግንባታው ኮንትራክተር የቲኤንቲ ኮንትራክሽንና የአማካሪው ድርጅት ባለሙያዎች የግንባታውን ሂደት በተመለከተ ለሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢው አምባሳደር ግርማ ብሩና ለአባላቱ ገለጻ አድርገዋል፡፡ ባለሙያዎቹ በገለጻቸው የሕንጻው የመዋቅር ሥራ 90 በመቶ የአጠቃላይ ግንባታው ሥራ ደግሞ…

ብሔራዊ የምርምር ስራዎች ግምገማ ተካሄደ

በኢትየጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የምርምርና ስልጠና ዘርፍ የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ አገር ዓቀፍ የምርምር ስራዎች ግምገማ መድረክ ተካሄደ። በዚህ ከህዳር 8 እስከ ህዳር 11 ቀን 2018ዓ.ም በወንጂ በተካሄደው የምርምር ስራዎች ግምገማ መድረክ ላይ ሰባት የምርምር ውጤቶች (ግኝቶች) እና 17 የምርምር ፕሮፖዛሎች ቀርበውና ውይይት ተደርጎባቸው ጸድቀዋል። ሰባቱ የምርምር ግኝቶች (ውጤቶች) በዝርያ ማሻሻል፣ በእርሻ ምህንድስና እና በአፈር ሳይንስ እንዲሁም በስኳር ቴክኖሎጂ እና ምሕንድና…

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

ሪፎርም እንዴት እንደሚሠራ ቋሚ ዐውደ ርዕይ የሚሆን ውጤት በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ተመለከትን። የወንጂ ስኳር ፋብሪካ የዛሬ ሰባ ዓመት ነበር በጥሩ መሠረት ላይ የተገነባው። ግን ከዘመን ጋር ካልተጓዙ መቅደም ብቻውን መብለጥን አያመጣም። ቀድሞ የበቀለን ጆሮ በኋላ የመጣ ቀንድ ሊቀድመው ይችላል። እየፈጠኑና እየፈጠሩ ዘመኑን ካልቀደሙት፣ ጊዜው ራሱ ይቀድማል። ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የዛሬ ሦስት ዓመት ለሠራተኞቹ ደሞዝ መክፈል ተስኖት ነበር። ዕዳ እንደ…

የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካን ወደሥራ ለማስገባት በአገዳ ልማት ላይ ጠንክሮ መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካን ወደሥራ ለማስገባት በአገዳ ልማት ላይ ጠንክሮ መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

አዲስ የተመደቡት የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ ከሠራተኞች ጋር ትውውቅ አድርገዋል ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ተግዳሮቶች ስኳር ማምረት ያቆመውን የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካን ወደ ምርት ሥራው መልሶ ለማስገባት የፋብሪካውን የአገዳ ሽፋን ለማሳደግ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዲንሳ አብደና የተመራ ቡድን ሰሞኑን በፋብሪካው በመከናወን ላይ የሚገኙ ልዩ ልዩ ተግባራትን ተዘዋውሮ በጎበኘትና…

ስኳር አካዳሚ መደበኛ ስልጠና መስጠት ጀመረ

ስኳር አካዳሚ መደበኛ ስልጠና መስጠት ጀመረ

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ስኳር አካዳሚ ፈቃድ ካገኘባቸው የስልጠና ዘርፎች በአራቱ መደበኛ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡ የአካዳሚው የመደበኛ ስልጠና ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአካዳሚው መሰብሰቢያ አዳራሽ መጋቢት 29 ቀን 2017ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ በዚሁ ወቅት በግሩፑ የምርምርና ስልጠና ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈታሚ አቶ አባይነህ ባዘዘው ባደረጉት የመግቢያ ንግግር የሰው ኃይል ሁለንተናዊ ብቃት ለምርትና ምርታማነት ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው አካዳሚው መደበኛ ስልጠና መጀመሩ ለኢትዮጵያ…

“ሥነ ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት” በሚል መሪ ቃል ለግሩፑ የሥራ መሪዎች ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው

“ሥነ ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት” በሚል መሪ ቃል ለግሩፑ የሥራ መሪዎች ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው

ለኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሥራ መሪዎች “ሥነ ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት” በሚል መሪ ቃል ሙስና እና ብልሹ አሠራሮችን ለመከላከል የሚያስችል ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው፡፡ የካቲት 25 ቀን 2017ዓ.ም በአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተጀመረውን ስልጠና በንግግር የከፈቱት የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ያዘጋጀው ይህ ስልጠና በሥነ ምግባር የታነጸ፣ ሙስናን…

ኢትዮጵያና ኩባ በስኳር ልማት ዘርፍ በጋራ ሊሰሩባቸው በተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

ኢትዮጵያና ኩባ በስኳር ልማት ዘርፍ በጋራ ሊሰሩባቸው በተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

የኩባ ስኳር ኢንዱስትሪ ዘርፍ የባለሙያዎች ቡድን             ያዘጋጀው የቴክኒካል ሰነድ ርክክብ ተከናወነ   _______________________________________ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙት የኩባ አምባሳደር ሜይሊን ሱዋሬዝ ከስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከክቡር አቶ ወዮ ሮባ እና የግሩፑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ሁለቱ አገራት በስኳር ልማት ዘርፍ በጋራ ለመስራት ቀደም ሲል በተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ ዙሪያ የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በግሩፑ ዋና መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ…

ግሩፑ የስኳር ኢንዱስትሪውን ወደላቀ ደረጃ የማሻገር ማዕከላዊ ሚናውን አጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል

ግሩፑ የስኳር ኢንዱስትሪውን ወደላቀ ደረጃ የማሻገር ማዕከላዊ ሚናውን አጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል

በግሩፑ የስድስት ወራት አፈጻጸም ላይ ውይይት ተደርጓል ___________________________________________________________________ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዘርፉን ወደላቀ ደረጃ የማሻገር ማዕከላዊ ሚናውን በመወጣት ረገድ እያከናወነው የሚገኘውን ተግባር የበለጠ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ አስታወቀ፡፡ በግሩፑ የስድስት ወራት አፈጻጸም ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የኬሚካል ፖርትፎሊዮ ዳይሬክተር ወ/ሮ አስማ ረዲ የካቲት 13 ቀን 2017ዓ.ም በግሩፑ ዋና መስሪያ ቤት የግሩፑ የስድስት ወራት አፈጻጸም በተገመገመበት…

በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3/1 ስኳር ፋብሪካ ዋና ከተማ የተገነቡ የመጠጥ ውሃ ቦኖዎች ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ

በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3/1 ስኳር ፋብሪካ ዋና ከተማ የተገነቡ የመጠጥ ውሃ ቦኖዎች ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3/1 ስኳር ፋብሪካ ዋና ከተማ የነበረውን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ የተገነቡ አምስት የመጠጥ ውሃ ቦኖዎች ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ፡፡ የመጠጥ ውሃ ቦኖዎቹ ታህሳስ 18 ቀን 2017ዓ.ም በፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ፈይሳ ፈቃዱ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን የፋብሪካው የሕዝብ ግንኙነትና ተሳትፎ የሥራ ክፍል ያደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡፡ ቦኖዎቹ ለአገልግሎት ክፍት ሲደረጉ ንግግር ያደረጉት የፋብሪካው…