• +251115526653
  • info@etsugar.com
  • Phillips Building, Chad St, Addis Ababa, Ethiopia
“ሥነ ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት” በሚል መሪ ቃል ለግሩፑ የሥራ መሪዎች ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው

“ሥነ ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት” በሚል መሪ ቃል ለግሩፑ የሥራ መሪዎች ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው

ለኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሥራ መሪዎች “ሥነ ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት” በሚል መሪ ቃል ሙስና እና ብልሹ አሠራሮችን ለመከላከል የሚያስችል ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው፡፡ የካቲት 25 ቀን 2017ዓ.ም በአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተጀመረውን ስልጠና በንግግር የከፈቱት የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ያዘጋጀው ይህ ስልጠና በሥነ ምግባር የታነጸ፣ ሙስናን…

ኢትዮጵያና ኩባ በስኳር ልማት ዘርፍ በጋራ ሊሰሩባቸው በተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

ኢትዮጵያና ኩባ በስኳር ልማት ዘርፍ በጋራ ሊሰሩባቸው በተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

የኩባ ስኳር ኢንዱስትሪ ዘርፍ የባለሙያዎች ቡድን             ያዘጋጀው የቴክኒካል ሰነድ ርክክብ ተከናወነ   _______________________________________ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙት የኩባ አምባሳደር ሜይሊን ሱዋሬዝ ከስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከክቡር አቶ ወዮ ሮባ እና የግሩፑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ሁለቱ አገራት በስኳር ልማት ዘርፍ በጋራ ለመስራት ቀደም ሲል በተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ ዙሪያ የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በግሩፑ ዋና መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ…

ግሩፑ የስኳር ኢንዱስትሪውን ወደላቀ ደረጃ የማሻገር ማዕከላዊ ሚናውን አጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል

ግሩፑ የስኳር ኢንዱስትሪውን ወደላቀ ደረጃ የማሻገር ማዕከላዊ ሚናውን አጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል

በግሩፑ የስድስት ወራት አፈጻጸም ላይ ውይይት ተደርጓል ___________________________________________________________________ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዘርፉን ወደላቀ ደረጃ የማሻገር ማዕከላዊ ሚናውን በመወጣት ረገድ እያከናወነው የሚገኘውን ተግባር የበለጠ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ አስታወቀ፡፡ በግሩፑ የስድስት ወራት አፈጻጸም ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የኬሚካል ፖርትፎሊዮ ዳይሬክተር ወ/ሮ አስማ ረዲ የካቲት 13 ቀን 2017ዓ.ም በግሩፑ ዋና መስሪያ ቤት የግሩፑ የስድስት ወራት አፈጻጸም በተገመገመበት…

በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3/1 ስኳር ፋብሪካ ዋና ከተማ የተገነቡ የመጠጥ ውሃ ቦኖዎች ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ

በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3/1 ስኳር ፋብሪካ ዋና ከተማ የተገነቡ የመጠጥ ውሃ ቦኖዎች ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3/1 ስኳር ፋብሪካ ዋና ከተማ የነበረውን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ የተገነቡ አምስት የመጠጥ ውሃ ቦኖዎች ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ፡፡ የመጠጥ ውሃ ቦኖዎቹ ታህሳስ 18 ቀን 2017ዓ.ም በፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ፈይሳ ፈቃዱ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን የፋብሪካው የሕዝብ ግንኙነትና ተሳትፎ የሥራ ክፍል ያደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡፡ ቦኖዎቹ ለአገልግሎት ክፍት ሲደረጉ ንግግር ያደረጉት የፋብሪካው…

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ የበጀት ዓመቱን የስኳር ምርት ሥራ ጀመረ

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ የበጀት ዓመቱን የስኳር ምርት ሥራ ጀመረ

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ የ2017ዓ.ም የስኳር ምርት ሥራውን በመጀመር ከታህሳስ 5 ቀን 2017ዓ.ም ጀምሮ ስኳር በማውጣት ላይ ይገኛል፡፡ የፋብሪካው የክረምት ጥገና ከተጠናቀቀ በኋላ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ፈይሳ ፍቃዱ፣ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በተገኙበት በደማቅ ሥነ ሥርዓት አገዳ የመፍጨት ሥራውን እንደጀመረም ተመላክቷል፡፡ በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የሚገኙት የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 እና 3…

እውቅና በተገኘባቸው የስልጠና መስኮች መደበኛ ስልጠና በማስጀመሪያና በስኳር ኢንዱስትሪ ምርምር ፍኖተ ካርታ ዙሪያ የምክክር ወርክሾ ተካሄደ

እውቅና በተገኘባቸው የስልጠና መስኮች መደበኛ ስልጠና በማስጀመሪያና በስኳር ኢንዱስትሪ ምርምር ፍኖተ ካርታ ዙሪያ የምክክር ወርክሾ ተካሄደ

አካዳሚው በምዘና ማዕከልነት እንዲሰራም ዕውቅና ተሰጥቶታል የኢትዮጵያ ስኳር አካዳሚ እውቅና ባገኘባቸው የስልጠና መስኮች መደበኛ ስልጠና በማስጀመሪያ እና በስኳር ኢንዱስትሪ ምርምር ፍኖተ ካርታ ዙሪያ የምክክር ወርክሾ ኅዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ተካሄደ፡፡ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባ የመሩትን የምክክር መድረክ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው የከፈቱት በግሩፑ የምርምርና ሥልጠና ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ…

የግሩፑ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች “የህልም ጉልበት ለዕምርታዊ ዕድገት” በሚል ርዕስ ውይይት አካሄዱ

ለኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች “የህልም ጉልበት ለዕምርታዊ ዕድገት” በሚል ርዕስ ለፌዴራል የመንግስት ተቋማት ሠራተኞች በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ማክሰኞ ህዳር 10 ቀን 2017ዓ.ም በአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ውይይቱን የመሩትና የተዘጋጀውን ሰነድ ያቀረቡት በግሩፑ የማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታፈሰ አሰፋ ባደረጉት ገለጻ፤ ውይይቱ ወቅታዊ፣ የመንግሥት ሠራተኛው መንግስት ምን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ግንዛቤ…

በስኳር ፋብሪካዎች በሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች የክልሉን ወጣቶች ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

በስኳር ፋብሪካዎች በሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች የክልሉን ወጣቶች ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

በኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች በሚፈጠሩ የስራ ዕድሎች የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ውይይት በአርባ ምንጭ ከተማ ጥቅምት 29 ቀን 2017ዓ.ም ተካሄደ፡፡ በውይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያረጉት የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለትና ሶስት ስኳር ፋብሪካዎች አካባቢን ለማልማትና የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መገንባታቸውን አብራርተዋል። ፋብሪካዎቹ በአሁኑ ሰአት 11 ሺህ ለሚደርሱ…

በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ተቀጥረው ከሚሰሩ የሱርማ ማሕበረሰብ አባላት ጋር ውይይት ተካሄደ

በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ተቀጥረው ከሚሰሩ የሱርማ ማሕበረሰብ አባላት ጋር ውይይት ተካሄደ

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ተቀጥረው በመስራት ላይ ከሚገኙ የሱርማ ማሕበረሰብ አባላት ጋር ጥቅምት 19 ቀን 2017ዓ.ም የአካባቢውን ጸጥታና ደህንነት በተመለከተ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ ላይ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1/3 ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ካሳ ተስፋዬ፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት እና ፌደራል ፖሊስ አመራር አካላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ ባደረጉት ንግግር…

ፋብሪካው ከአካባቢው አርብቶ አደር ማህበረሰብ ጋር ውይይት አደረገ

ፋብሪካው ከአካባቢው አርብቶ አደር ማህበረሰብ ጋር ውይይት አደረገ

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1/3 ስኳር ፋብሪካ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ልማት ፕሮጀክት በሚገኝበት አካባቢ ነዋሪ ከሆኑ የቦዲ ማህረሰብ አባላት ጋር ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ጸጥታ እና ደህንነነትን እንዲሁም የሸንኮራ አገዳ ልማት ሥራውን በተመለከተ ውይይት አደረገ፡፡ በውይይቱ የማህበረሰቡ ባላባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የመስተዳደር አካላት እንዲሁም በፋብሪካው በቋሚነትና በጊዜያዊነት በመስራት ላይ የሚገኙ የማህበረሰቡ ተወላጅ የደህንነትና ጥበቃ፣ የጋራዥ ሠራተኞች እና ኦፕሬተሮች ተሳታፊ…