Tenders/Bid

የጨረታ ማስታወቂያ ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የጨረታ ቁጥር LP/OT/04/SIG/2016/17
- የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ለ2017 በጀት ዓመት የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ሎቶች በዘርፉ የተሰማሩ ትራንስፖርት ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
-
- ሎት-1 የተለያዩ ዕቃዎችን ወደ ተለያዩ ቦታዎች ለማጓጓዝ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ
- ሎት-2 ከኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካ ወደ ወንጂ ሸዋ እና ገፈርሳ ስኳር ማጓጓዝ አገልግሎት ግዥ
- ሎት-3 ከፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ ወደ አዲስ አበባ ስኳር ማጓጓዝ አገልግሎት ግዥ
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ ለ2016/17 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስ/ በጨረታ መሳተፍ እንዲችል የተሰጠ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No.) ሠርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች/አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን/መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ብር ሶስት መቶ) በብር በመክፈል ወይም በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000000888862 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00፣ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ
አድራሻ አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ
ጨለለቅ አልሳም ህንጻ ፊት ለፊት
ፊሊፒስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220
ስልክ ቁጥር +251 11 5516271 ወይም 115-500417፣
አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ሎት-1 ከቀኑ 8፡30 ሰዓት፤ ሎት-2 ከቀኑ 9፡00 ሰዓት፤ እና ሎት-3 ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለስኳር ሎት-1 ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ፣ለሎት -2 ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) እና ለሎት -3 ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተመሠከረለት ቼክ (CPO) ከቴክኒክ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለዘጠና (90) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
admin
0