ዜናዎች

የስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አመራር አባላትና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም አከናወኑ
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አመራር አባላት እና ሠራተኞች በዘንድሮው ዓመት “ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ተግባራዊ ለማድረግ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ገላን ኮንዶሚኒዬም አካባቢ በመገኘት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሄዱ፡፡
በዚሁ ግሩፑ ባከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ላይ ችግኝ በመትከል አሻራቸውን ያኖሩት የስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባ በፕሮግራሙ ማጠናቀቂያ ላይ ባደረጉት ንግግር ስኳር ፋብሪካዎች እና ፕሮጀክቶች የአካባቢ ጥበቃ ሥራን እንደ አንድ ዋና ተግባራቸው በማከናወን ረገድ የዳበረ ልምድ እንዳላቸው አመልክተው የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብርም ከዋና መስሪያ ቤት በተጨማሪ በሁሉም ስኳር ፋሪካዎች እና ፕሮጀክቶች መከናወኑን አመልክተዋል፡፡
የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር በአገር አቀፍ ደረጃ 500 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀንበር ለመትከል ያለመ ነው፡፡
admin
0














