ዜናዎች

በበጀት ዓመቱ የመንግስት የመጀመሪያ ስድስት ወር የዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አመራር አባላትና ሰራተኞች በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወር የመንግስት የዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ማክሰኞ መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ውይይት አድርገዋል፡፡
ሜክሲኮ አደባባይ በሚገኘው የአዲስ አበባ መስተዳድር ፍትህ ቢሮ መሰብሰቢያ አዳራሽ የመንግስት የመጀመሪያ ግማሽ በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ዝርዝር ሪፖርት ቀርቦ ነው ውይይት የተደረገበት፡፡
በዚሁ የውይይት መድረክም የ2016 በጀት ዓመት ሃገራዊ አፈፃፀም ዝርዝር ሪፖርት፣ የሃገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀምና የልዩ ልዩ ዘርፎች አፈፃፀም፣ የማኑፋክቸሪንግ እና የአምራች ዘርፉ አፈፃፀም በተለይም ደግሞ የስኳር ዘርፉ ያለበት ሁኔታ፣ የሰብል ምርት በተለይም በስንዴና በሌሎች የልማት ዘርፎች የተገኘው ውጤት አበረታች ሆኖ ከዋጋ አንፃር ለውጡ ያልታየው ለምንድን ነው በሚሉና በወደፊት የመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጎ መግባባት ላይ በመድረስ የዕለቱ የውይይት መድረክ ተጠናቋል፡፡:
admin
0