ዜናዎች

የኩባ የስኳር ኢንዱስትሪ የቴክኒክ ቡድን ኦሞ ኩራዝ ገባ
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ከኩባ አቻው አዝኩባ ግሩፖ አዙካሬሮ መንግስታዊ የስኳር ኩባንያ ጋር በትብበር ለመስራት በተፈራረመው የመግባቢያ ስምምነት መሠረት ወደኢትዮጵያ የመጣው ሰባት አባላት ያሉት የቴክኒክ ቡድን በመተሐራ እና በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች የነበረውን ቆይታ አጠናቆ በኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች ዛሬ ሥራውን ጀምሯል፡፡
ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ እና ሦሥት ስኳር ፋብሪካዎች ጽሕፈት ቤት በተደረገ ውይይት የፋብሪካዎቹ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥበቡ ማሞ ለቴክኒክ ቡድኑ የፋብሪካውን አጠቃላይ ሁኔታ አስመልክተው ገለጻ አድርገዋል፡፡
የቴክኒክ ቡድኑ በፋብሪካ ኦፕሬሽንና በእርሻ ኦፕሬሽን የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚያግዙ የመፍትሔ ሐሳቦችን እንደሚያቀርብ ያላቸውን እምነትም ዋና ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡
የቴክኒክ ቡድኑ ከፋብሪካው የዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጆች ጋር በየዘርፋቸው ያሉ ችግሮችን አስመልክተው ውይይት አድርገዋል፡፡
admin
0