• +251115526653
  • info@etsugar.com
  • Phillips Building, Chad St, Addis Ababa, Ethiopia
ዜናዎች
የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች ወደተሻለ የምርት አፈጻጸም ለመሸጋገር  ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል

የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች ወደተሻለ የምርት አፈጻጸም ለመሸጋገር  ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል

  • ለኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች የሥራ መሪዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ተጀምሯል

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ስር የሚገኙት የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች ወደተሻለ የምርት አፈጻጸም ለመሸጋገር ከፍተኛ ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባ አስገነዘቡ፡፡

ክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚው መስከረም 23 ቀን 2017ዓ.ም የተጀመረውንና ለኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች የሥራ መሪዎች የተዘጋጀውን የአቅም ግንባታ ስልጠና በንግግር ሲከፍቱ እንደገለጹት ፋብሪካዎቹ  ያሉባቸውን የውስጥ ችግሮቻቸውን ፈትተው ወደተሻለ የምርት አፈጻጸም ለመሸጋገር በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎችን ከሁኔታዎች ጋር አስማምቶ ውጤታማ ለማድረግ ከበቂ በላይ የመማሪያ ጊዜ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ወዮ ፋብሪካዎቹ ለዕቅዶቻቸው አለመሳካት ውጪዊ ምክንያቶችን ከመደርደር ይልቅ ወደውስጣቸው መመልከት የሚጠበቅባቸው ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሳቸውን አስገንዝበዋል፡፡

አያይዘውም ከፍተኛ የማምረት አቅም ያላቸው የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች አሁን ያሉበት ሁኔታ ውስጥ የሚገኙት ማምረት የሚገባቸውን ያህል ምርት ማምረት ባለመቻላቸው መሆኑን የሥራ መሪዎችና ሰራተኞች ተረድተው ወደራሳቸው መመልከትና የውስጥ ችግሮቻቸውን ለመፍታት ከወትሮው የተለየ ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

ለፋብሪካዎቹ የሥራ መሪዎች መሰጠት የተጀመረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ሁሉም ራሱን አይቶ ካሉበት ችግሮች ለመላቀቅ ድፍረት የተሞላበት ምልከታ የሚያደርግበትና ራሱን ለማሻሻል ጥረት ማድረግ የሚጀምርበት ሊሆን እንደሚገባም ነው ዋና ሥራ አስፈጻሚው ያስገነዘቡት፡፡

ክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚው “የለውጥ ዕድሎችና ፈተናዎች እንዲሁም ስጋቶች” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ የመወያያ ጽሑፍ አቅርበውም ሰልጣኞች ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡