• +251115526653
  • info@etsugar.com
  • Phillips Building, Chad St, Addis Ababa, Ethiopia
ዜናዎች
ለሥራ መሪዎች መሰጠት የተጀመረው ስልጠና እንደቀጠለ ነው

ለሥራ መሪዎች መሰጠት የተጀመረው ስልጠና እንደቀጠለ ነው

ትናንት የተጀመረውና ለኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች የሥራ መሪዎች በመሰጠት ላይ የሚገኘው የአቅም ግንባታ ስልጠና ዛሬም ቀጥሏል፡፡

በዛሬው የጠዋት መርሐ ግብር “የለውጥ ዕድሎችን የመጠቀም ብቃት፡- የአመራር ምንነት፣ ዕድገት፣ ባሕሪያትና ተግዳሮቶች” በሚል ርዕስ የመነሻ ሐሳብ የግሩፑ የኮርፖሬት ጉዳዮች ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት በአቶ ዘመድኩን ተክሌ ቀርቧል፡፡

ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው የአመራር ብቃት ፣ የእውነተኛ መሪ መርሆዎች፣ መሪዎች የሚያነሷቸው ጥያቄዎች፣ የመሪና የተከታይ ስጋቶች፣ የአመራር ስልቶች እና የመሪ ሚና ምንድን ነው በሚሉ ንዑስ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከነዚህ ርዕሰ ጉዳዮች አንጻር የፋብሪካዎቹ የሥራ መሪዎች ራሳቸውን ማየትና መፈተሸ እንደሚገባቸው እንዲሁም ራሳቸውን ማስተካከል እንደሚገባም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎችም በአምስት ቡድኖች ተከፍለው በቀረበው የመነሻ ሐሳብ ላይ ተመስርቶ በተዘጋጁ የመወያያ ነጥቦች ላይ ውይይት አድርገው፣ የየቡድኖቹ የውይይት ሪፖርት ቀርቦ አቅጣጫ ተሰጥቶበት የዕለቱ መርሐ ግብር ተጠናቋል፡፡