• +251115526653
  • info@etsugar.com
  • Phillips Building, Chad St, Addis Ababa, Ethiopia
ዜናዎች
ፋብሪካው በሰው ኃይል አቅርቦት ዙሪያ እያጋጠመው ያለውን ችግር መፍታት የሚያስችል ውይይት ከክልሉ ቢሮ ጋር አካሄደ

ፋብሪካው በሰው ኃይል አቅርቦት ዙሪያ እያጋጠመው ያለውን ችግር መፍታት የሚያስችል ውይይት ከክልሉ ቢሮ ጋር አካሄደ

በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3/1 ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ በአቶ ሚጀና ቢቂላ የተመራ የፋብሪካው የማኔጅመንት ቡድን ፋብሪካው በጉልበት ሠራተኛ የሰው ኃይል አቅርቦት ረገድ እየጋጠመው ያለውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችለውን ውይይት ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የአሰሪና ሰራተኛ ዘርፍ ኃላፊ ከአቶ አብዮት ሸጋ እና ከአሪ ዞን ሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ከወ/ሮ አንለይ እርገጤ ጋር ሰኔ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ተወያዬ፡፡

በዚሁ ጂንካ ከተማ በተካሄደ ውይይትም ከጉልበት ሠራተኛ አቅርቦት በተጨማሪ በሠራተኞች አያያዝና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን የፋብሪካው ቀጣይ የምርት ጊዜ ሥራ የተሳለጠ እንዲሆን መግባባት ላይ መደረሱንና ለፋብሪካው የምርት ሥራ ስኬት ሁሉም አካላት በጋራ እንደሚሰሩ አቅጣጫ መቀመጡን የፋብሪካው የሕዝብ ግንኙነትና ተሳትፎ የሥራ ክፍል አመልክቷል፡፡

የፋብሪካው የ2018 ዓ.ም የምርት ወቅት ከመጀመሩ በፊትም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ የጋራ የውይይት መድረክ እንደሚመቻችና የጋራ ዕቅድ ወጥቶም ወደ ምርት እንደሚገባ ዘገባው ጨምሮ ገልጿል፡፡