
ግሩፑ ማዕድ አጋራ
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ለሚገኙ አቅመ ደካሞች ማዕድ አጋራ፡፡
የ2016 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በተከናወነ የማዕድ ማጋራት ሥነ ሥርዓት በወረዳው ለሚገኙ አቅመ ደካሞች ዱቄትና ዘይት ድጋፍ ተደርጓል፡፡
ግሩፑ 146‚700.00 (አንድ መቶ አርባ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ብር) ወጪ በማድረግ የገዛውን 550 ኪሎ ግራም ዱቄትና 570 ሊትር ዘይት ለወረዳው ሥራ አስፈጻሚ ለአቶ በላይ ቆዬ አስረክቧል፡፡
በማዕድ ማጋራቱ ላይ ግሩፑን በመወከል የተገኙት የሥነ ምግባርና መልካም አስተዳደር መምሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ደረሰ ካሳዬ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያዊ ባሕል የሆነውን በበዓል ወቅት መጠያየቅና መረዳዳት አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡
ግሩፑ ማሕበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች አካባቢ ለሚገኙ የማሕበረሰብ ክፍሎች በመስኖ የሚለማ ውሃ ገብ መሬት አዘጋጅቶ፣ የመንገድ መሠረተ ልማት እንዲሁም የሰውና የእንስሳት ጤና ጣቢያዎችን እና ትምህርት ቤቶችን ገንብቶ ለአገልግሎት ማብቃቱን ሥራ አስኪያጁ አታውሰው በዛሬው ዕለትም በወረዳው ለሚገኙ አቅመ ደካሞች ያደረገው የማዕድ ማጋራት አንዱ ማሳያ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ግሩፑ በዓሉን በማስመልከት መሰል ድጋፎችን አቅም በፈቀደ መልኩ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስረድተዋል፡፡
በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 10 ሥራ አስፈጻሚ አቶ በላይ ቆዬ ግሩፑ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በቀጣይም በልዩ ልዩ መስኮች ከግሩፑ ጋር ተቀራርበው እንደሚሰሩም አስታውቀዋል፡፡



