
የኦሞ ኩራዝ የአገዳ ልማት ማሻሻልን አስመልክቶ በቀረበ ምክር ሐሳብ ላይ ውይይት ተደረገ
የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች የአገዳ ሽፋን ለማሳደግና ምርታማነትን ለማሻሻል በቀረበ ምክረ ሐሳብ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
ሐምሌ 4 ቀን 2016ዓ.ም የተደረገውን ውይይት በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባ የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎችን የአገዳ ሽፋን ለማሳደግና ምርታማነትን ለማሻሻል ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
የፋብሪካዎቹን የአገዳ ሽፋን ማሳደግና ምርታማነትን ማሻሻል ፋብሪካዎቹ በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚው በንግግራቸው ጠቁመዋል፡፡
የግሩፑ የትራንስፎርሜሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሳምሶን ወልቀባ ለምክክር በተዘጋጀው ምክረ ሐሳብ ላይ የተጠቀሱ ስትራቴጂካዊ የሆኑ ቁልፍ ጉዳዮችን እና ስትራቴጂካዊ ያልሆኑ ጉዳዮችን ለተሳታፊዎች አቅርበው በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ አቅጣጫ የሰጡት የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባ በእጃችን የሚገኙ ማሽኖችን ጠግነን እና ያሉንን ሀብቶች አቀናጅተን የመሬት ዝግጅት ሥራዎችን ማፋጠን የምንችልባቸውን አማራጮች ማየት ተገቢ ነው ብለዋል፡፡
ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ማሽኖች ግዥ በአፋጣኝ እንዲፈጸምም አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
በምክረ ሐሳቡ ላይ በተግዳሮትነት ለተጠቀሱ ጉዳዮች የሚመለከታቸውን ክፍሎች ለይተው ሥራውን በኃላፊነት እንዲሰሩ የቤት ሥራ ሰጥተው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡