• +251115526653
  • info@etsugar.com
  • Phillips Building, Chad St, Addis Ababa, Ethiopia
ዜናዎች
በኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካ በድሮን ቴክኖሎጂ የታገዘ የአገዳ አብሳይ ኬሚካል ርጭት ተካሄደ

በኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካ በድሮን ቴክኖሎጂ የታገዘ የአገዳ አብሳይ ኬሚካል ርጭት ተካሄደ

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነው የሸንኮራ አገዳ ማብሰያ ኬሚካል (Ripner) ርጭት በድሮን ቴክኖሎጂ በመታገዝ በኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች ማሳ ላይ መካሄድ ተጀመረ፡፡

ይህ ቴክኖሎጂ በስኳር ፋብሪካዎቹ አካባቢ ያለውን የሸንኮራ አገዳ የስኳር ይዘት በከፍተኛ መጠን በማሻሻል ዓመታዊ የስኳር ምርትን ወደ ላቀ ደረጃ ያደርሳል ተብሎ ይታመናል፡፡

የግሩፑ የምርምርና ስልጠና ዘርፍም አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመዳሠሥ እና በሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ተግባራዊ የሚሆንበት አግባብ በዘርፉ የምርምር ባለሙያዎች ጥናት ተደርጎ ነው ወደሥራ የተገባው፡፡

በዚህም ዘርፉ በኦሞ ስኳር ፋብሪካዎች የማረጋገጫ ሙከራ /Verification Trial/ ለመስራት ባቀደው መሠረት በአራት የተለያዩ ማሳዎች (በ16 ሄክታር ማሳ ላይ) የተለያዩ አገዳ አብሳይ ኬሚካሎችን እና በተለያየ የእድገት ደረጃ ላይ ያሉ የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎች ላይ ርጭቱ ተከናውኗል፡፡

በቀጣይም በማረጋገጫ ሙከራው የሚገኝ ውጤትን መሠረት በማድረግ በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ እና በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር /INSA/ መካከል በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት መሠረት ቴክኖሎጂው በ1‚000 ሄክታር ማሳ ላይ በቀጣይ የምርት ወቅት በስፋት የሚተገበር ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *