• +251115526653
  • info@etsugar.com
  • Phillips Building, Chad St, Addis Ababa, Ethiopia
ዜናዎች
ለኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች የሥራ መሪዎች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ

ለኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች የሥራ መሪዎች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች የሥራ መሪዎች ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ከመስከረም 23 እስከ መስከረም 26 ቀን 2017ዓ.ም በዘለቀው በዚህ የሥራ መሪዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና የለውጥ ዕድሎችና ፈተናዎች እንዲሁም ስጋቶች፣ የለውጥ ዕድሎችን የመጠቀም ብቃት መገንባት፡- የአመራር ምንነት፣ ዕድገት ባሕሪያትና ተግዳሮቶች፣ የቡድን መንፈስ ግንባታ አስፈላጊነት፣ ስልቶችና ፈተናዎች፤ አሠራሮችን የበለጠ ሳይናሳዊ ማድረግ፡- የተቋም ሥራ አፈጻጸምን ማዘመንና ማሻሻል፣ የዕውቀትና የልምድ ልውውጥ አሰራር መዘርጋት፣ ተቋማዊ ባሕል መገንባት እና ውጤታማ ስብሰባዎችን ማካሄድ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ስልጠና በተሰጠባቸው በሁሉም ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የስልጠናው ተሳታፊዎች በቡድን ተከፋፍለው ውይይት አድርገውባቸዋል፡፡ በቡድን ውይይታቸውም ርዕሰ ጉዳዮቹን ከራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር በመዳሰስ ሪፖርት አቅርበዋል፤ በቀረቡት ሪፖርቶች ላይም የማጠቃለያ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ንግግር ያደረጉትና አቅጣጫ ያስቀመጡት የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባ የፋብሪካዎቹ የሥራ መሪዎች ከሥልጠናው ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት ተጠቅመው የፋብሪካዎቹን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ተግተው መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡:

የተሰጠው ስልጠና ውጤት አምጥቷል የሚባለው ያገኘናነውን ዕውቀትና የፈጠረልንን መነሳሳት  በፋብሪካዎቻችን የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ስንጠቀምበት በመሆኑ ከዛሬ ጀምሮ የሥራ መሪዎች ተግባራዊ በማድረግ አርዓያ መሆን ይጠበቅብናል ብለዋል ክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚው፡፡

ስልጠናው የ2016 የዕቅድ አፈጻጸምን በአግባቡ ለመገምገምና ፋብሪካዎቻችን ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ ለመረዳት እንዲሁም የ2017 የኦፕሬሽን አፈጻጸምን የተሻለ ለማድረግ የጎላ ሚና ያለው በመሆኑ የሥራ መሪዎች ከስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት በተዋረድ ለሁሉም ሠራተኞችም ማካፈል እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡