ዜናዎች

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ የበጀት ዓመቱን የስኳር ምርት ሥራ ጀመረ
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ የ2017ዓ.ም የስኳር ምርት ሥራውን በመጀመር ከታህሳስ 5 ቀን 2017ዓ.ም ጀምሮ ስኳር በማውጣት ላይ ይገኛል፡፡
የፋብሪካው የክረምት ጥገና ከተጠናቀቀ በኋላ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ፈይሳ ፍቃዱ፣ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በተገኙበት በደማቅ ሥነ ሥርዓት አገዳ የመፍጨት ሥራውን እንደጀመረም ተመላክቷል፡፡
በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የሚገኙት የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 እና 3 ስኳር ፋብሪካዎች በአካባቢው ካለው የአየር ንብረት ጋር በተያያዘ የማምረቻ ጊዜያቸው በዓመት ሁለት ጊዜ መሆኑ ይታወሳል፡፡
Assegid Tesfaye
0







